ፕሬዝዳንት ባይደን ለመጀመሪያ ግዜ  አታሲምስ የተባለውን የረጅም-ርቀት ሚሳኤል ዩክሬን በሩሲያ ግዛቶች ላይ እንድትጠቀም ፈቀዱ

ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ባይደን ለመጀመሪያ ግዜ  አታሲምስ የተባለውን የረጅም-ርቀት ሚሳኤል ዩክሬን በሩሲያ ግዛቶች ላይ እንድትጠቀም ፈቀዱ ስማቸው ያልተገለፀ ምንጮች ለኒዎርክ ታይምስ እንደነገሩት፦ በዚህ ውሳኔ ላይ የባይደን አማካሪዎች የተከፋፈሉ ሲሆን ፤ ውሳኔው ከሁለት ወር በኋላ ስልጣን የሚይዙት ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለዩክሬን የሚደረግ ድጋፍን ለመቀነስ ቃልበገቡ ማግስት የተደረገ ነው። የተወሰኑ የፔንታጐን ሀላፊዎች የሚሳኤሉን ለዩክሬን መላክ አሜሪካ ጦር ብዙ አቅርቦት የለውም በማለት ተቃውመውታል። የተወሰኑ የኋይትሀውስ ሰራተኞች በምላሹ ሩሲያ ጦርነቱን የበለጠ ትገፋበታለች በማለት ሰጋታቸውን ገልፀዋል። የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት መሳሪያዎች በሩሲያ መሬት ላይ የሚሞከሩ ከሆነ አሜሪካም ሆነ የኔቶ አባላት ከሩሲያ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ጦርነት ይገባሉ በማለት አስጠንቅቀዋል። ፑቲን እንዳስረዱት የዩክሬን ጦር ራሱን ችሎ እንደዚህ አይነት የረጅም-ርቀት መሳሪያዎችን መጠቀም አይችልም ፤ ምእራባውያን የስለላ እና ኢላማዎች በተመለከተ እንዲሁም ቀጥተኛ የሆነ የኔቶ ባለሙያ እገዛ ካላደረገላቸው በስተቀር።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ   ስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ  @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0