ሶስት የአፍሪካ የቁንጅና ንግስቶች በ2024 ሚስ ዩኒቨርስ ውድድር ፍጻሜ ላይ ደመቁ

ሰብስክራይብ
ሶስት የአፍሪካ የቁንጅና ንግስቶች በ2024 ሚስ ዩኒቨርስ ውድድር ፍጻሜ ላይ ደመቁ ሚስ ናይጄሪያ ቺዲማ አዴትሺና ቅዳሜ ዕለት በሜክሲኮ ሲቲ በተካሄደው የ2024 ሚስ ዩኒቨርስ ውድድር ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ተወዳዳሪ ሆናለች።"የተስፋ ምልክት፣ የእምነት ብርሃን ሆኜ እዚህ ቆሜያለሁ። በጸጋ የጸናሁ ሰው እንደመሆኔ መጠን ለራሴ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም እንደታገልኩ አምናለሁ" ስትል የ23 ዓመቷ የሕግ ተማሪ በውድድሩ ወቅት ተናግራለች።ከናይጄሪያዊ አባቷ እና ከሞዛምቢካዊ እናቷ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ አቅራቢያ በሶዌቶ ነው የተወለደችው። የ34 ዓመቷ ሚስ ግብጽ ሎጂና ሳላህ፣ ሌላኛዋ ለውድድሩ ፍጻሜ የደረሰች ሞዴል ናት። ይህች ወጣት እናት ባጋጠማት ለምጽ የተባለ የቆዳ ህመም ምክንያት በልጅነቷ ከባድ ጊዜን አሳልፋለች። የ28 አመቷ ሚስ ዙምባቡዌይ ሳክሂሌ ዱብ በብሄራዊ የመዋቢያ ውድድር ላይ የታዳሚያኑን ቀልብ ሰንቃ ይዛ ነበር። "የንስር ከፍታ" ብላ በሰየመችው መዋቢያ የዙምባቡዌን ቁንጅና አስመስክራለች። ክንፎቹ በቪክቶሪያን ፏፏቴ ላይ ያለውን ቀስተደመና ሲያመላክቱ የድንጋይ ላይ ምስሎቹ  ታላቋን ዙምባቡዌ ያመላክታሉ።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ   ስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ  @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0