በሩሲያ እየተሰጠ ያለው የህክምና ስልጠና አፍሪካውያኑ ዶክተሮች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቁጥር እንዲቀንስ ይረዳል ተባለ "እነሱ የሚያደርጉትን ማድረግ ከቻልን ተመሳሳይ ውጤት እንደምናገኝ ሩሲያ ጥሩ የስኬት ምሳሌ ነች" ይህንን ለስፑትኒክ አፍሪካ የተናገሩት ከዛምቢያ ፣ ዙምባብዌ እና ሩዋንዳ ለተወጣጡ ዶክተሮች በሩሲያ ሞስኮ ከህዳር 3-16 እየተሰጠ ያለውን የተቀናጀ የእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ላይ ያተኮረ የሩሲያ የህክምና ስልጠና እየወሰዱ ያሉት የህፃናት ስፔሻሊስቷ በዛምቢያ ሴቶች እና አዲስ የተወለዱ ህፃናት ሆስፒታል የምትሰራው ራቼል ቾምባ ናት።በሩሲያ የወሰድነው ሰልጠና አፍሪካውያን ስፔሻሊስቶች በጣም የሚጠቅመን ነው ፤ በተሻሻለው የወሊድ እና የጨቅላ ህፃናት እንክብካቤ ዙሪያ በተለየ የወሰድነው በጣም ይጠቅመናል በማለት የዙምባቡዌ የህፃናት ሀኪም የሆኑት ዶርካስ ሙቴድ ተናግረዋል። አክለውም ሀገሯ ዙምባቡዌ የተወሰኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመውሰድ እና ያሉ አሰራሮችን በጥራት ለማስኬድ እንደማሳያ አዲስ ለተወለዱ ህፃናት አስቀድሞ የተስተካከለ የአየር ግፊት ማስተካከያ መጠቀምን እና የመሳሰሉትን ለመከተል እቅድ መኖሩን አሳውቀዋል። " የተወሰኑት እዚ በተግባር ያየናቸው እዛም እንተገብራቸዋለን ፤ ነገርግን አፅነኦት መስጠት ያለብን ለምን እንደሚያስፈልገን ነው" በማለት የህፃናት ሀኪሟ አስረድተዋል።ፕሮግራሙ ትኩረት ያደረገው ለአፍሪካ "ዕዳ" የሆነውን የእናቶችና የጨቅላ ሕፃናት ሞት መቀነስ ላይ መሆኑን በዛምቢያ የሴቶችና ሕፃናት ሆስፒታል የጽንስና የማህጸን ሐኪም የሆኑት ኢማንጋ ኢካቦንጎ ተናግረዋል። "እኔ እንደማስበው ከሩሲያ የመጡ ባለሙያዎች ሁሉንም ነገር ማድረግ አይችሉም፤ ግን እኛ እዚህ የተማርነውን ዕውቀት መውሰድ እንችላለን፣ ስለዚህ እኛ ከስራችን ያሉትን እና ሌሎች ሰዎችን አገር ቤት ማስተማር እንችላለን፤ በዚህም የእናቶችን ሞት እንዴት መቀነስ እንደምንችል ማየት እንችላለን" ሲሉ ኢካቦንጎ ገልጸዋል።የሩሲያ ስፔሻሊስቶች እናቶችን እና አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናትን በሚረዱበት ጊዜ የሚፈጸሙ አንዳንድ ስህተቶችን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል አስረድተዋል ሲሉ በሩዋንዳ በማዋለድ የአሥር ዓመት ልምድ ያላት ትዊዚዪማና ፍራንሶይስ ዣቪየር ጠቅሰዋል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በሩሲያ እየተሰጠ ያለው የህክምና ስልጠና አፍሪካውያኑ ዶክተሮች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቁጥር እንዲቀንስ ይረዳል ተባለ
በሩሲያ እየተሰጠ ያለው የህክምና ስልጠና አፍሪካውያኑ ዶክተሮች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቁጥር እንዲቀንስ ይረዳል ተባለ
Sputnik አፍሪካ
በሩሲያ እየተሰጠ ያለው የህክምና ስልጠና አፍሪካውያኑ ዶክተሮች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቁጥር እንዲቀንስ ይረዳል ተባለ "እነሱ የሚያደርጉትን ማድረግ ከቻልን ተመሳሳይ ውጤት እንደምናገኝ ሩሲያ ጥሩ የስኬት ምሳሌ ነች"... 17.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-17T18:23+0300
2024-11-17T18:23+0300
2024-11-17T18:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
በሩሲያ እየተሰጠ ያለው የህክምና ስልጠና አፍሪካውያኑ ዶክተሮች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቁጥር እንዲቀንስ ይረዳል ተባለ
18:23 17.11.2024 (የተሻሻለ: 18:44 17.11.2024)
ሰብስክራይብ