የኮንጎ ህዝብ ህገመንግስቱን እንዲሻሻል መወሰን አለበት በማለት ፕሬዝዳንቱ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የኮንጎ ህዝብ ህገመንግስቱን እንዲሻሻል መወሰን አለበት በማለት ፕሬዝዳንቱ ተናገሩ "በሚቀጥለው አመት ሁሉን አሳታፊ የሚሆን ብልህ ሴት እና ወንድ ዜጎች የሚካተቱበትን ኮሚቴ አቋቁሜ ህገመንግስቱን እንዲገመግሙ አድርጋለሁ። የስራው እቅድ ለእናንተ ለሀገሬ ህዝቦች የሚቀርብ ይሆናል ፤ አስፈላጊ ከሆነ ህዝቡ እናማክራለን ፤ ስለዚህ ህዝቡ ራሱ ማሻሻያውን የሚፈልግ እንዲሁም መለወጥ የሚፈልግ መሆኑን ወይም ማሻሻያው እንዲቆም መፈለጉን የሚወስን ይሆናል" በማለት ፕሬዚዳንት   ፊሊክስ ተሰኬደ ተናግሯል። ፕሬዝዳንቱ አሁን ያለው ህገመንግስት በተለይም አንቀፅ 217 የሀገሪቷን ሉአላዊነት የሚገዳደር ነው በማለት  የህገመንግስቱን ማሻሻያ እንደሚደግፉ ያስታወቁ ሲሆን ፤ አንቀፅ 217 የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ መንግስት የሀገሪቷን ሉአላዊነት በከፊል ሊገዳደር የሚችል ስምምነቶችን "የአፍሪካን ህብረት ለማጠናከር" በሚል ልትፈርም ትችላለች የሚል ሀሳብ አለው። "ለህዝባችን ንቃተ ህሊና እና ብልህነት ስድብ ነው ፤ ለአፍሪካ ሀገሮች ተብሎ ሉአላዊነታችን እንዲደፈር የሚፈቅደውን እና ዝነኛውን አንቀፅ 217  የያዘዉን ህገመንግስት እንዲያሻሽሉ የኮንጎን ህዝቦች መጠየቅ" በማለት ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ ደቡብ-ምስራቅ በምትገኘው ሉቡምባሺ ለህዝቡ ባደረጉት ንግግር አስረድተዋል። በቅዳሜው ንግግራቸው ወቅት ተሰኬደ በተቃዋሚዎቻቸው ህገመንግስቱን መቀየር የሚፈልጉት በሁለት ጊዜ የተገደበዉን የፕሬዝዳንትነት የስልጣን ቆይታ ለማሻሻል ነው የሚለውን ሀሳብ አስተባብለዋል። " ለዘላለም በስልጣን ላይ ለመቆየት እና ህዝቤን ለማሰቃየት አልመጣሁም። በፍፁም ይህንን አላረግም። የማስበዉ ፣ የማደርገው ሁሉ ለህዝቤ ደስታ እና ለሀገሬ ልማት" ነው በማለት አፅንኦት ሰጥቶ ተናግሯል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ   ስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ  @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0