ሶስት የሩሲያ እና አንድ የቤላሩስ ዜጋ በቻድ ከሚገኝ እስርቤት ከሳምንታት ቆይታ በኋላ ተለቀቁ

ሰብስክራይብ
ሶስት የሩሲያ እና አንድ የቤላሩስ ዜጋ በቻድ ከሚገኝ እስርቤት ከሳምንታት ቆይታ በኋላ ተለቀቁ ከታሳሪዎቹ አንዱ የነበረው የሶሾሎጂስቱ ማክሲም ሹጋሌ የስራ ባልደረባ "ሶስት የሩሲያ እና አንድ የቤላሩስ ዜጋ በቻድ ለሁለት ወር ያህል በእስርቤት ከቆዩ በኋላ ተለቅቀው ዛሬ ማታ ሞስኮ ገብተዋል"  በማለት ለስፑትኒክ ተናግሯል።ባለፈዉ መስከረም 19 የተያዙትን የሩሲያ እና የቤላሩስ ዜጎች አስመልክቶ በወቅቱ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከእስር መፈታታቸው እስኪረጋገጥ ድረስ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፆ ነበር። የሹጋሌ የስራ ባልደረባ ለስፑትኒክ ጨምሮም በተያዙበት እለት እንዳናገራቸው ነገርግን በኢንጃሜና አየር ማረፊያ ከደረሰ በኋላ ድንበሩን ማለፍ እንዳልቻለ አስረድቷል።  ባለፈዉ መስከረም 25 በሩሲያ የቻድ አምባሳደር የሆኑት አደም ባቺር ፦  የቻዱ ፕሬዚዳንት መሀመት ኢድሪስ ዴቢ እስረኞቹ እንዲፈቱ መወሰናቸውን ለስፑቲኒክ ተናግሮ ነበር።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ   ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ  @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0