በአሜሪካ የመጀመሪያው ክሌድ አንድ ኤምፖክስ በሽታ መመዝገቡን የካሊፎርኒያ ኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል ገለጸ

ሰብስክራይብ
በአሜሪካ የመጀመሪያው ክሌድ አንድ ኤምፖክስ በሽታ መመዝገቡን የካሊፎርኒያ ኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል ገለጸ  "የካሊፎርኒያ ኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል፤ ለአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የመጀመሪያው በክሌድ አንድ ኤምፖክስ (የዝንጀሮ ፈንጣጣ)  በሽታ የተያዘ ሰው መመዝገቡን  ሪፖርት አድርጓል። ክሌድ አንድ  ከክሌድ ሁለት የተለየ ሲሆን ከጎርጎሮሳውያኑ 2022 ጀምሮ በካሊፎርኒያ እና አሜሪካ ውስጥ ሲሰራጭ የቆየ የኤምፖክስ ዝርያ ነው። ግለሰቡ በቤት ውስጥ ተለይቶ የሚገኝ ሲሆን ለኅብረተሰብ ያለው ስጋት በጣም ዝቅተኛ ነው" ሲል የጤና ትምህርት ክፍሉ ባወጣው መግለጫ ገልጿል። የመጀመሪያው በበሽታው ተጠቂ በቅርቡ ከምስራቅ አፍሪካ የመጣ ግለሰብ ሲሆን ግለሰቡ ወደ አሜሪካ ከተመለሰ በኋላ ወዲያው በአካባቢው በሚገኝ ጤና ተቋም ውስጥ ህክምና ተደርጎለት መውጣቱን ትምህርት ክፍሉ አስታውቋል። ቀደም ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ በአፍሪካ የተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ ዓለም አቀፍ የህዝብ ጤና ስጋት መሆኑን አውጀዋል።የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) በአህጉሪቱ በተከሰተው የኤምፖክስ ወረርሽኝ ምክንያት በጎርጎሮሳውያኑ ነሐሴ 13  የህዝብ ጤና ስጋት መሆኑን በማወጅ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ክትባቶችን ለማሰባሰብ ድጋፍ እንዲያደግ ጥሪ አቅርቧል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንቡብ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ   ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ  @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0