የማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የተጣለባት የኪምበርሌ ሂደት ያልተጣራ የዳይመንድ ንግድ እግድ ከ 11 አመት በኋላ ተነሳላት

ሰብስክራይብ
የማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የተጣለባት የኪምበርሌ ሂደት ያልተጣራ የዳይመንድ ንግድ እግድ ከ 11 አመት በኋላ ተነሳላት   አለምአቀፍ የዳይመንድ ንግድን የሚቆጣጠረው እና የሚከታተለው  የኪምበርሌ የማህበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት እገዳው ያለፈው አርብ መነሳቱን በመግለጫው አስታውቋል። በፕሬዝዳንት ፍራንስዋ ቦዚዜ ላይ የተደረገው መፈንቀለ-መንግስት ተከትሎ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር 2013 የተጣለው የውጭ ንግድ እገዳ በ2015 እና በ2018 የወሰነው የእገዳው ክፍል ተነስቶ ነበር። ነገርግን ከተመዘገቡት 24 የማእድን ማውጫዎች ሁለት ሶስተኛው በእገዳው ስር ነበሩ። " ይህ ውሳኔ የኪምበርሌ ጥምረት ሀላፊነት ማለቁን አያሳይም ፤ ጥምረቱ ሆነ የማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የዳይመንድ ንግድ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ማጭበርበሮችን ፣ ግጭቶችን  እና ድህነት  ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች ላይ አብረው ይሰራሉ። በተጨማሪም ይህ ውሳኔ ሰብአዊ መብቶች የሚከበሩበት ፍትህ የሚረጋገጥበት ፣ አነስተኛ የማእድን አውጪዎች የሚደገፉበት፣ የዳይመንድ የኮንትሮባንድ ንግዶች የሚቀሩበት እና የዳይመንድ የማእድን ስፍራዎች የሚለሙበት ጊዜ አዲስ ጅማሮ ይሆናል" በማለት መግለጫው ያትታል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንቡብ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይ ስልኮች APK ፋይል ሊንክ   ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ  @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0