ዩኔስኮ በጋዜጠኞች ደህንነት ዙርያ በቅርቡ ይፋ ያደረገው ሪፖርት በፀረ-ሩሲያ አመላካከቱ ተተቸ

ሰብስክራይብ
ዩኔስኮ በጋዜጠኞች ደህንነት ዙርያ በቅርቡ ይፋ ያደረገው ሪፖርት በፀረ-ሩሲያ አመላካከቱ ተተቸ የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሪ አዙላይ፤ እ.ኤ.አ. ከ2022 እስከ 2023 የጋዜጠኞች ደህንነት እና የገዳዮቻቸውን አለመጠየቅ አስመልክቶ ይፋ ባደረጉት ረቂቅ ሪፖርት ዙርያ አስተያየቱን የሰጠው የሩሲያ ስቴት ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ብሮድካስቲንግ ኩባንያ፤ ሪፖርቱን ፖለቲካዊ እና ጭፍን ጥላቻ ነው ሲል ገልጿታል። በምዕራባውያን ጋዜጠኞች ላይ ያተኮረው ሪፖርት፤ በቅርብ ዓመታት የተገደሉ እና የተጎዱ ሩሲያውያን ጋዜጠኞችን በዝርዝሩ ውስጥ ሳያካት ቀርቷል ሲል ብሮድካስተሩ ገልጿል። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፤ ሪፖርቱን "ለዘረኝነት የተቃረበና ግልጽ የሆነ አድልዎ" ነው ብለው፤ የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሪ አዙለይ ኃላፊነታቸውን ችላ ብለዋል በማለት ከሰዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0