የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2024 የቢዝነስ ተጓዦች ሽልማት የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ ተመረጠ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2024 የቢዝነስ ተጓዦች ሽልማት የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ ተመረጠ "የ2024ቱን የቢዝነስ ተጓዦች ሽልማት ለተከታታይ አምስት ዓመታት በማግኘታችን ደስተኞች ነን። ይህ ሽልማት የቡድን አባላቶቻችንን እና ተልዕኳችንን ያለችግር እንድንፈጽም ከእኛ ጋር ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሰሩ ባለድርሻ አካላትን ቁርጠኝነት፣ ትጋት እና ልፋት የሚያረጋግጥ ነው" ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ተናግረዋል። ቢዝነስ ትራቭለር፤ ለስራ ወደ ውጭ ሀገር የሚበሩ ተጓዦችን ትኩረቱ ያደረገ በዓለም የታወቀ መጽሔት ነው። በመጽሔቱ ይፋ የሚደረገው አሸናፊ አብዛኛውን ግዜ በአንባቢዎች ድምጽ እና በገለልተኛ የኦዲት ኩባንያ ይወሰናል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0