ኢትዮጵያ ውስጥ በ9 ወር ከ7.

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ውስጥ በ9 ወር ከ7.3 ሚልዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ እንደተያዙ እና 1,157 ሰዎች መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጤና ኤጀንሲ ይፋ ያደረገው ሪፖርት፤ በወባ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ካለፉት ሰባት ዓመታት ወዲህ ከፍተኛው እንደሆነ አሳይቷል። 75% የሚሆነው የኢትዮጵያ ክፍል ለበሽታው ተጋላጭ እንደሆነ የገለጸው የዓለም ጤና ድርጅት፤ ወባ የከፋ ችግር ደቅኗል ብሏል።እ.አ.አ 2024 በአራት ክልሎች ብቻ፤ 81 በመቶ በበሽታው የተያዙ ሰዎች እና 89 በመቶ ሞት እንደተመዘገበ ድርጅቱ አስታውቋል። እነዚህም ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች እንደሆኑ ተገልጿል። በኢትዮጵያ ምዕራባዊ ክፍል ከፍተኛ የወባ በሽታ ስርጭት መከሰቱም ተመላክቷል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0