የሩሲያ የሰብዓዊ ትብብር ኤጀንሲ በዛምቢያ እና ታንዛኒያ የትምህርት ማዕከላትን ከፈተ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ የሰብዓዊ ትብብር ኤጀንሲ በዛምቢያ እና ታንዛኒያ የትምህርት ማዕከላትን ከፈተ የትምህርት አሰጣጡ በሉሳካ እና ዳሬሰላም የሩሲያ ባህል ማዕከላት ውስጥ በሚገኙ፤ የሮሶትሩድኒቼስትቮ የማሟያ ማስተማሪያ ክፍሎች መካሄድ ጀምሯል። ማዕከላቱ፤ ከሩሲያ ቀዳሚ አምራቾች በተገኙ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ትምህርታዊ የቤት ዕቃዎች እና መሳሪያዎች እንዲሁም ትምህርታዊ፣ የማስተማሪያ ዘዴዎች፣ ማጣቀሻ እና የልቦለድ መጽፍቶች የተሟሉ ናቸው። በትምህርት ማዕከላቱ፤ በሩሲያ ቋንቋ ትምህርት ይሰጣል፣ የሩሲያ ዩንቨርስቲዎች የጥናት ውጤቶች ይቀርባሉ እንዲሁም በሩሲያ መንግሥት ኮታ መሰረት በሩሲያ ለሚማሩ እጩዎች ምክር ይካሄዳል። የማዕከላቱ ዋና ዓላማ፤ ከሩሲያ ዋና ዋና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የአፍሪካ ወጣቶች የተጨማሪ ትምህርት ፕሮግራሞችን እንዲያገኙ ማድረግ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0