በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለው ታሪካዊ ግንኙነት በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መጠናከር እንዳለበት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለስልጣን አስታወቁ

ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለው ታሪካዊ ግንኙነት በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መጠናከር እንዳለበት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለስልጣን አስታወቁ "ሩሲያ–ኢትዮጵያ፡ የምንጠብቀው ጊዜ የለም!" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ተካሄዶ የነበረው ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ መድረክ ተጠናቋል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፤ "የሀገራቱ ታሪካዊ ግንኙነት በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ የበለጠ ሊጠናከር ይገባል" ብለዋል። "የምዕራባውያን ሀገራት የዓለም ንግድን እየዘጉ፣ እያፈራረሱ እና እያዳከሙ ካሉበት ስርዓት በመውጣት፤ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን፤ በተለይም ከብሪክስ ሀገራት ጋር ትብብራችንን ውጤታማ ሊያደርጉ የሚችሉ መንገዶችን መፈለግ ያስፈልጋል" ሲሉ በፎረሙ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና በሩሲያ ክሬሚያ ሪፐብሊክ ለሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ቋሚ ተወካይ የሆኑት አምባሳደር ጆርጂ ሙራዶቭ፤ ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጠቁመዋል። በፎረሙ ላይ ከተገኙት የሩሲያ የንግድ ተወካዮች አንዱ የሆኑት የፔኔትሮን ኩባንያ ፕሬዝዳንት ኢጎር ቼርኖጎሎቭ፤ "አዲስ ክፍያ ስርዓት ያስፈልገናለን" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል። "ዶላርን መጠቀም ማቆም በጣም ጥሩ ነገር ነው" ብለዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0