የእስራኤል ጦር ጄቶች በሶሪያ መዲና ደማስቆ ማዕከል በሚገኘው ማዜህ አካባቢ ላይ ጥቃት አደረሱ

ሰብስክራይብ
የእስራኤል ጦር ጄቶች በሶሪያ መዲና ደማስቆ ማዕከል በሚገኘው ማዜህ አካባቢ ላይ ጥቃት አደረሱ በደማስቆ የስፑትኒክ ዘጋቢ የላከው ዘገባ፡- የሲቪል መከላከያ እና የእሳት አደጋ መከላከያ ክፍሎች በምእራብ ማዜህ አካባቢ የእስራኤል ሚሳኤል ጥቃት ወደደረሰበት ቦታ በፍጥነት ደርሰዋል። ሶስት ሚሳኤሎች በአካባቢው በሚገኝ አንድ አፓርትመንት ህንጻ ደብድበዋል። በእስራኤል የአየር ጥቃት ሶስት ሰዎች የሞቱ እና የቆሰሉ ቢኖሩም፤ ትክክለኛው ቁጥር አሁንም በመጣራት ላይ ይገኛል። ጥቃቱ በደማስቆ ቁድሳያ የመኖሪያ አካባቢ በሚገኝ አንድ አፓርትመንት ላይ ከደረሰው የእስራኤል የአየር ጥቃት ጋር የተገጣጠመ ነበር። በጥቃት ብዙ ሰዎች መቁሰላቸውን ዘገባዎች አረጋግጠዋል።ምስሉቹ የስፑትኒክ ናቸውዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0