ፈረንሳይ፤ በአልጄሪያ ያካሄደችው የኒውክሌር ሙከራ ተፈጥሮ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ሲሉ የአዘርባጃኑ ፕሬዝዳንት ተናገሩ

ሰብስክራይብ
ፈረንሳይ፤ በአልጄሪያ ያካሄደችው የኒውክሌር ሙከራ ተፈጥሮ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ሲሉ የአዘርባጃኑ ፕሬዝዳንት ተናገሩ የአዘርባጃን ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ፤ ተመሳሳይ ችግር በፈረንሳይ ፖሊኔዥያ እንደተፈጠረ ጨምረው ገልፀዋል። "ፈረንሳይ ባካሄደችው በርካታ የኒውክሌር ሙከራዎች ምክንያት የፈረንሳይ ፖሊኔዥያ ተፈጥሮ በከፍተኛ ደረጃ ተመናምኗል። በደሴቶቹ ላይ ለደረሰው የአፈር ብክለት እና ጉዳት ተጠያቂ ነች። ፈረንሳይ በቅኝ አገዛዟ ወቅት በአልጄሪያ ያካሄደቻቸውን 17 የኒውክሌር ሙከራዎች ከግምት ውስጥ ካስገባን በፕላኔታችን ሥነ-ምህዳር ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት መገመት ይቻላል" ሲሉ ከ29ው የኮፕ ጉባኤ ጎን ለጎን ተናግረዋል። ጉባኤው፤ በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ እየተካሄደ ሲሆን፤ ወደ 80 የሚጠጉ የሀገር መሪዎች እና መንግሥታት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0