ቱርክ ከእስራኤል ጋር የነበራት ግንኙነት አቋረጠች "በሬሲፕ ታይፕ ኤርዶአን የሚመራው የቱርክ ሪፐብሊክ መንግሥት ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት አይቀጥልም። ከእስራኤል ጋር የነበረንን ንግድ እና ግንኙነት ሙሉ በሙሉ አቋርጠናል። ከፍልስጤም ተገቢ ዓላማ ጎን እስከ መጨረሻው በፅናት እንቆማለን" ሲሉ የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶአን ከሳዑዲ አረቢያ እና አዘርባጃን ሲመለሱ አውሮፕላን ውስጥ ለጋዜጠኞች ጥያቄ መልስ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል። ቱርክ፤ በጋዛ ሰርጥ የእስራኤል ጥቃት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፤ የቴል አቪቭን ድርጊት ስታወግዝ እና እስራኤል በፍልስጤም ሲቪሎች ላይ የጅምላ ግድያ እየፈጸመች ነው ስትል ትከሳለች። ሀገሪቱ በተደጋጋሚ የተኩስ አቁም ጥሪ ስታቀርብ እና በእስራኤል ላይ ጫና ስታደርግም ቆይታለች። በግንቦት ወር መጀመሪያ፤ የቱርክ የንግድ ሚኒስቴር ከእስራኤል ጋር የነበረው የንግድ ልውውጥ ሙሉ በሙሉ መቆሙን አስታውቋል። አንካራ፤ ቀደም ብላ ወደ እስራኤል የሚላኩ 54 ሸቀጣ ሸቀጦችን ገድባለች።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ቱርክ ከእስራኤል ጋር የነበራት ግንኙነት አቋረጠች
ቱርክ ከእስራኤል ጋር የነበራት ግንኙነት አቋረጠች
Sputnik አፍሪካ
ቱርክ ከእስራኤል ጋር የነበራት ግንኙነት አቋረጠች "በሬሲፕ ታይፕ ኤርዶአን የሚመራው የቱርክ ሪፐብሊክ መንግሥት ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት አይቀጥልም። ከእስራኤል ጋር የነበረንን ንግድ እና ግንኙነት ሙሉ በሙሉ አቋርጠናል። ከፍልስጤም ተገቢ ዓላማ... 14.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-14T12:43+0300
2024-11-14T12:43+0300
2024-11-14T13:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий