የህዳር 5 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የህዳር 5 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 ሩሲያ ከአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ናት ሲሉ፤ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ተናገሩ። 🟠 የእስራኤል ጦር ጄት በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻ በሺያክ አካባቢ ሶስት ከባድ ጥቃቶችን ፈጸመ። 🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ ስልጣን ከመልቀቃቸው በፊት ለዩክሬን ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ኮንግረስን እንደሚጠይቁ፤ የአሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን ተናገሩ። 🟠 የአውሮፓ ፓርላማ ረዳቶች ሃሰተኛ ቅጥርን በተመለከተ ክስ የተመሰረተባቸው የፈረንሳይ ፖለቲከኛ ማሪን ለፔን፤ ከምርጫ ፉክክር እንዲታገዱ አቃቤ ህግ ጠየቀ። 🟠 አንድ ግለሰብ በብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በብራዚል ተወካዮች ምክር ቤት ህንጻዎች አካባቢ ሁለት ፍንዳታዎችን ፈጸመ። በመኪና ማቆሚያ ውስጥ መኪና ካፈነዳ በኋላ ፈንጂዎችን ወደ ፍርድ ቤቱ ህንጻ በመወርወር፤ መግቢያው ላይ እራሱን እንዳጠፋ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 የሩሲያ የጸጥታ ሃይሎች በማሪፑል የዩክሬን ወታደራዊ ማከማቻ፤ ከ3 ቶን በላይ ለመድኃኒት ምርት የሚውሉ ንጥረ ነገሮችን እንዳገኙ፤ የዶንዬትስክ ህዝባዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት የፕሬስ አገልግሎት አስታውቋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0