የህዳር 4 ምሽት አበይት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን በስልክ የተወያዩ ሲሆን በኦፔክ ፕላስ የተቀራረበ ቅንጅት አስፈላጊ እንደሆነ እንዲሁም የሚወሰዱ እርምጃዎች ውጤታማ እና ፈጣን መሆን እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል። 🟠 የዩክሬን ጦር በዛፖሮዢያ ክልል ኢነርጎዳር ላይ በተከታታይ በፈጸመው ጥቃት በትንሹ 8 ፍንዳታዎች መመዝገባቸውን እና አንድ ሰው መሞቱን የከተማዋ ከንቲባ አስታውቀዋል። 🟠 ከ100 በላይ የቤልጂየም ገበሬዎች የአውሮፓ ኮሚሽን ከላቲን አሜሪካ ሀገራት ጋር ለመፈራረም ያሰበውን የነጻ ንግድ ስምምነት እንደሚቃወሙ ገለፁ። 🟠 የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በታደሰው የኖትርዳም ካቴድራል ውስጥ የመክፈቻ ንግግራቸውን ሊያደረጉ ነው መባሉ ካስተቻቸው በኋላ ንግግራቸውን ወደ በረንዳው ቀይረዋል። 🟠 የሚቀጥለው ዓመት በሰው ልጅ ታሪክ በጣም ሞቃታማው ይሆናል ሲሉ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናገሩ። 🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬን እና ሩሲያን ግጭት ለማስቆም ለዩክሬን ልዩ መልዕክተኛ ይሾማሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል የአሜሪካ ሚዲያ ዘግቧል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የህዳር 4 ምሽት አበይት የዓለም ዜናዎች፦
የህዳር 4 ምሽት አበይት የዓለም ዜናዎች፦
Sputnik አፍሪካ
የህዳር 4 ምሽት አበይት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን በስልክ የተወያዩ ሲሆን በኦፔክ ፕላስ የተቀራረበ ቅንጅት አስፈላጊ እንደሆነ እንዲሁም የሚወሰዱ እርምጃዎች ውጤታማ እና... 13.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-13T20:54+0300
2024-11-13T20:54+0300
2024-11-13T21:24+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий