የህዳር 4 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፡-

ሰብስክራይብ
የህዳር 4 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፡-🟠 የእስራኤል አየር ሃይል ጄቶች፤ በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻ ሀሬት ሂሪክ አካባቢ 2 ጥቃቶችን ፈጽመዋል።🟠 ዩናይትድ ስቴትስ፤ ሶሪያ በሚገኝና በኢራን በሚደገፍ ቡድን የጦር መሳሪያ እና ሎጅስቲክስ ተቋማት ላይ ጥቃት እንዳደረሰች፤ የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ አስታውቋል።🟠 ኒጀር የሩሲያ ኩባንያዎች ዩራንየምን ጨምሮ፤ በሀገሪቱ የሚገኙ የተፈጥሮ ሃብቶችን እንዲያስሱ እና እንዲያወጡ መጋበዟን፤ የኒጀር ማዕድን ሚኒስትር ኦስማን አባርቺ ተናግረዋል።🟠 የስፔስ ኤክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤለን መስክ እና ነጋዴው ቪቬክ ራማስዋሚ፤ በዩናይትድ ስቴትስ የመንግሥትን ብቃት የሚገመግም አዲስ መስሪያ ቤት እንደሚመሩና መሥርያ ቤቱ ዶጅ እንደሚባል፤ ዶናልድ ትራምፕ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።🟠 የሩሲያ አየር መከላከያ ሌሊቱን 29 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በሩሲያ ክልሎች ማውደሙን፤ የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0