ሩሲያ በ2025 በአፍሪካ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሚውል 500 ሚሊዮን ሩብልስ ለመመደብ አቀደች ይኽ በጀት የሶስት አመቱ እቅድ አካል ነው

ሰብስክራይብ
ሩሲያ በ2025 በአፍሪካ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሚውል 500 ሚሊዮን ሩብልስ ለመመደብ አቀደች ይኽ በጀት የሶስት አመቱ እቅድ አካል ነው የሚመደበው  በጀት ለአፍሪካ ሀገራት የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ሲሆን በተለይ በሩሲያ መንግስት ለተመረጡ ድርጅቶች በድጎማ መልክ ማዋልን ያካትታል።ይህ ተነሳሽነት ሩሲያ ላላት ከፍተኛ የማዕድን ሀብት ማረጋገጫ ነው ሲሉ የተፈጥሮ ሀብት ሚንስቴር ኃላፊው አሌክሳንደር ኮዝሎቭ አጽንዕኦት ሰጥተዋል።  አክለውም የሩሲያ ከፍተኛ የጋዝ፣ የአልማዝ፣ የኒኬል፣ የኮባልት፣ የወርቅ፣ የብር፣ የፕላቲኒየም እና የአይረን ክምችት እንዲሁም ሌሎች ወሳኝ ማዕድናት እንዳሏት በመግለጽ በመስኩም በዓለም ላይ መሪ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል።ኮዝሎቭ የሩሲያ የጂኦሎጂ ኩባንያ የሆነውን ሮስጂኦን በመጥቀስ፤ በቤኒን፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ አንጎላ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ ቀድሞውኑ በመካሄድ ላይ ላሉ ፕሮጀክቶች እና በዚምባብዌ፣ አልጄሪያ፣ ቻድ፣ ሞዛምቢክ፣ ሴራሊዮን እና ማሊ ለታቀዱ ተጨማሪ ፕሮጀክቶች ያለቸውን ቁርጠኝነት እንደ ምሳሌ ጠቅሰዋል።እንደ ኮዝሎቭ ገለጻ፤  ሩሲያ የዓለም አቀፍ ገበያዎችን ለመቆጣጠር ያቀደ የሀብት ጥምረት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ለመፍጠር እየሰራች ነው። ይህ ተነሳሽነት በሩሲያ ቁጥጥር ስር ባለው  55 በመቶ የአልማዝ፣ 46 በመቶ የፓላዲየምና 23 በመቶ የወርቅን ጨምሮ  ከፍተኛ ክምችት እንዲሁም ከበርካታ የአፍሪካ ሀገሮች ጋር አጋርነት በመፍጠር የፕላቲኒየም፣ የኮባልት፣ የፎስፈረስ እና የዚርኮን ክምችት ድርሻ በመያዝ የሚደገፍ ነው ተብሏል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0