የመጀመሪያው የ #ሩሲያአፍሪካ አጋርነት ፎረም የሚንስትሮች ኮንፈረንስ የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 አላማ  እንዲሳካ ያነቃቃል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ
የመጀመሪያው የ #ሩሲያአፍሪካ አጋርነት ፎረም የሚንስትሮች ኮንፈረንስ የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 አላማ  እንዲሳካ ያነቃቃል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር" ዶክተር ጌዲዩን ለረጅም ጊዜ የቆየውን የሩሲያ- አፍሪካ ታሪካዊ ግንኙነት ያስታወሱ ሲሆን ፤ ይህንን የ #ሩሲያአፍሪካ አጋርነት መድረክ ፦ የአፍሪካ ህብረትን አጀንዳ 2063 ለማስፈፀም ይጠቅማል" ማለታቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤክስ ገፁ አስፍሯል። ጌዲዩን ጢሞትዩስ ጨምረው እያደገ የመጣው የ ሩሲያ እና አፍሪካ ግንኙነት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው። ሚኒስትሩ አክለውም በሳይንስ ፣ በቴክኖሎጂ ፣በግብርና እና ኢንዱስትሪ መስኮችም ትብብር ማድረግ ጠቃሚ ነው ብለዋል። ሩሲያ በተመድ ፀጥታ ምክርቤት የሚደረጉ ለውጦችን በተለይም በምክርቤቱ የተወከሉ ሀገራትን ቁጥር በመጨመር ረገድ የምታደርገውን አስተዋፆ ኢትዩጵያ በመልካም ትቀበላለች በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0