ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገሮች ብሄራዊ ገንዘቦችን ለንግድ እና ለፋይናንስ ልውውጦች መጠቀም ያለው አስፈላጊነት ላይ አፅንኦት ሰጥተውበታል የጋራ መግለጫው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ከ #ሩሲያአፍሪካ ሚኒስትሮች ኮንፈረስ የጋራ የአቋም መግለጫ ላይ የተወሰዱ ናቸው። ሶስተኛው የ #ሩሲያአፍሪካ የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ በ ጎርጎሮሳዊያኑ 2026 ይደረጋል አሸባሪነትን እና አክራሪነት ለመዋጋት አፍሪካ እና ሩሲያ በከፍተኛ ባለስልጣናት የሚመራ ውይይት እንዲኖር ዝግጁነታቸውን ገልፀዋል። አፍሪካ እና ሩሲያ በአፍሪካ ህብረት እና መስል የፀጥታ እና የትብብር ተቋማት መሀከል የሚኖር መስተጋብር ወሳኝ መሆኑን ተረድተዋል። አፍሪካ እና ሩሲያ የተሻለ የአለም አሰራር እንዲሁም በአለምአቀፍ ደረጃ ሰላም እና ፀጥታ እንዲኖር ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳካውን ስትራቴጂካዊ መተባበር፤ ሀገራት እኩል የመልማት እድል፣ የራሳቸውን ባህል እና ጥንታዊ ስልጣኔ ካላቸው የፖሎቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ የማህበረሰብ ስሪት ፣ ሰነምድራዊ አቀማመጥ እና የወታደራዊ አቅማቸው ሳይታይ እኩል አስኪታዩ ድረስ ይቀጥሉበታል። ሉአላዊ ሀገራት እኩል እስኪታዩ ፣ በዉስጥ ጉዳያቸው ጣልቃ አለመግባት ፣ የግዛት አንድነታቸው እንዲጠበቅ ማድረግ እና የህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብታቸው ድረስ ሀላፊነት በሚሰማው መልኩ አዲሰ የአለም አሰራር እንዲፈጠር አፍሪካ እና ሩሲያ ይሰራሉ። የውጭ ጉዳይ በተመለከተ ከአፍሪካ ህብረት እና ሌሎች ቀጠናዊ ህብረቶች ጋር አብሮ መስራት አፍሪካ እና ሩሲያ ቅድሚያ የሚሰጡት የልማት እና የገንቢ አጋርነት ሂደት ነው። ' ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች' የሚለው መርህ በመግለጫው አፅንኦት ተሰጥቶበታል ግጭቶችን በመፍታት ዙሪያ በተለየ። የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በአለም ኢኮኖሚ ውስጥ አፍሪካ ያላትን ውክልና ተፅእኖ ለማስፋፋት ዝግጁ መሆናቸው ተናግረዋል። በባህል ልውውጥ ዙርያ ያለው የ አፍሪካ እና ሩሲያ ትብብር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው። አፍሪካ እና ሩሲያ በአካባቢ እና የአየር ፀባይ ለውጥ ዙሪያ ያላቸው ትብብር በተመድ የሚደገፉ መድረኮችን ከማበረታታት በተጨማሪ የጉዳዩን ፖሎቲካዊ ይዘት እንዳይኖረው በመስራት ነው።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገሮች ብሄራዊ ገንዘቦችን ለንግድ እና ለፋይናንስ ልውውጦች መጠቀም ያለው አስፈላጊነት ላይ አፅንኦት ሰጥተውበታል የጋራ መግለጫው
ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገሮች ብሄራዊ ገንዘቦችን ለንግድ እና ለፋይናንስ ልውውጦች መጠቀም ያለው አስፈላጊነት ላይ አፅንኦት ሰጥተውበታል የጋራ መግለጫው
Sputnik አፍሪካ
ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገሮች ብሄራዊ ገንዘቦችን ለንግድ እና ለፋይናንስ ልውውጦች መጠቀም ያለው አስፈላጊነት ላይ አፅንኦት ሰጥተውበታል የጋራ መግለጫው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ከ #ሩሲያአፍሪካ ሚኒስትሮች ኮንፈረስ የጋራ የአቋም መግለጫ ላይ የተወሰዱ... 11.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-11T17:27+0300
2024-11-11T17:27+0300
2024-11-11T17:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገሮች ብሄራዊ ገንዘቦችን ለንግድ እና ለፋይናንስ ልውውጦች መጠቀም ያለው አስፈላጊነት ላይ አፅንኦት ሰጥተውበታል የጋራ መግለጫው
17:27 11.11.2024 (የተሻሻለ: 17:44 11.11.2024)
ሰብስክራይብ