ሩሲያ እንደ ቡርኪና ፋሶ ላሉ ሀገራት የኑክሌር ኃይል አቅርባለች ሲሉ የቡርኪና ፋሶ ከፍተኛ ዲፕሎማት ገለፁ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ እንደ ቡርኪና ፋሶ ላሉ ሀገራት የኑክሌር ኃይል አቅርባለች ሲሉ የቡርኪና ፋሶ ከፍተኛ ዲፕሎማት ገለፁ"ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ሩሲያ ላበረከተችው ሚና እውቅና መስጠት እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም ለበርካታ አሥርተ ዓመታት የኑክሌር ኃይል እንደ ቡርኪና ፋሶ ያሉ ሀገሮች ሊገዙት የማይችሉት ነገር ሆኖ ቀርቧል። ምስጋና ለሙዱላር ሪአክተር ይሁንና ዛሬ እንደ ቡርኪና ፋሶ ያሉ ሀገራት ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ኢኮኖሚያቸውን መደገፍ እንደሚችሉ ተገንዝበናል"  ሲሉ የቡርኪናፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካራሞኮ ትራኦሬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገለጹ።ሚኒስትሩ ይህን ያሉ እሁድ ዕለት በተካሄደው የመጀመሪያው #የሩሲያአፍሪካ የሚኒስትሮች አጋርነት ፎረም ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ነው። የቡርኪና ፋሶው ከፍተኛ ዲፕሎማት አክለውም፤ ሀገራቸው ኢንዱስትሪን የሚያንቀሳቅሱ የኃይል መሰረተ ልማቶችን ለመፍጠር እንደምትፈልግ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ በዚህ ፕሮጀክት ላይ ስለ ሩሲያ ኩባንያዎች ተሳትፎ ለመናገር ጊዜው ገና ነው ብለዋል። አነስተኛ ሞዱላር ሬአክተሮች ሩሲያ ካሳካቻቸው ታላላቅ ስኬቶች መካከል አንዱ መሆኑንም ዲፕሎማቱ ጠቅሰዋል።የመጀመሪያው #የሩሲያአፍሪካ የሚኒስትሮች አጋርነት ፎረም ኮንፈረንስ ከጥቅምት 30 እስከ ህዳት 1 በሩሲያዋ ሲሪዩስ ፌዴራል ግዛት በሶቺ ከተማ ተካሂዷል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0