የአፍሪካ ሀገራት በውጭያዊ ጫናዎች ወቅት በጽናት ቆመዋል ሲሉ የሲሸልስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጹ

ሰብስክራይብ
የአፍሪካ ሀገራት በውጭያዊ ጫናዎች ወቅት በጽናት ቆመዋል ሲሉ የሲሸልስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጹ "በሶቺው #ሩሲያአፍሪካ የሚኒስትሮች ኮንፍረንስ ላይ የተገኘነው ሀገራት ሊኖርብን የሚችለውን ጫና ችላ በማለት በሁለት እግራችን ለመቆም ስለምንፈልግ ነው ኮንፈረንሱን የተካፈልነው" ሲሉ  የሲሸልስ የውጭ ጉዳይና ቱሪዝም ሚኒስትር  ሲልቬስትሬ ራዴጎንዴ ለስፔትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ራዴጎንዴ፣ ሲሸልስ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ሲገልጹ ፤ በግልጽ ውይይትና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ አጋርነት ነው ብለዋል። "እኛ ሉዓላዊ ሀገር ነን፣ ትንሽም ነን፣ ነገር ግን አቋም መዉሰድ ሲያስፈልገን በራሳችን ብቻ አቋም ስለምንወስድ ኩራት ይሰማናል" በማለት የተናገሩር ሚንስትሩ፤ አልፎ አልፎ ልዩነቶች ቢኖሩም እንዲህ ዓይነቱ አጋርነት በሁለቱ አገሮች መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0