እንደ አፍሪካውያን ከማንም ትምህርት ሳንቀበል ችግሮቻችንን በራሳችን መፍታት እንፈልጋለን ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
እንደ አፍሪካውያን ከማንም ትምህርት ሳንቀበል ችግሮቻችንን በራሳችን መፍታት እንፈልጋለን ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናገሩ“ከማንም ውጭያዊ አካል ትምህርት ሳንቀበል” የአፍሪካ መፍትሄዎች ለአፍሪካ ችግሮች ያስፈልጋሉ ሲሉ የቡርኪና ፋሶ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ካራሞኮ ዥያን ማሬ ትራኦሬ  በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ እየተካሄደ ባለው የመጀመሪያው #ሩሲያአፍሪካ የሚንስትሮች አጋርነት ፎረም ኮንፍረንስ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። “ቡርኪናፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር በዚህ መንፈስ የሳሀል ሃገራት ኮንፌዴሬሽንና ጥምረት በመፍጠራችን ይህንን ራዕይ ለመደገፍ እዚህ ተገኝተናል። ይህ በህዝባችን የሚደገፍ በሀገራችን መሪዎች የሚመራ ሂደት ነው፣ እንዲሁም ለአገራቱ  ሁኔታ የሚስማማ አማራጭ እና መሳሪያ ነው። እናም እያጋጠመን ላለው ሁኔታ የተሻለው ምላሽ ነው ብለን በማመናችን ምክንያት ይህንን አማራጭ ለመደገፍ አቅደናል” ሲሉ ለስፑትኒክ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ገልጸዋል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0