ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የትምህርት አጋርነት ለማሳደግ ዝግጁ መሆንዋን የሩሲያው ምክትል ሚኒሰቴር ገለፁ

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የትምህርት አጋርነት ለማሳደግ ዝግጁ መሆንዋን የሩሲያው ምክትል ሚኒሰቴር ገለፁ " የሩሲያን መምህራን በዉጭ ሀገራት ልኮ ማስተማር ላይ ጥሩ ልምድ አለን፤ በዚህም የሩሲያ ትምህርት ቋንቋ እና ባህል በሌሎች አጋር ሀገሮች እንዲተዋወቅ ምክንያት ሆኗል ። በአፋሪካ በተለይ በስፋት እየሰራንበት ነው። አሁን ላይ በስድስት የአፍሪካ ሀገራት ይሄንን ፕሮጀክት እየሰራን ሲሆን ለማስፋፋት ዝግጁ ነን።" ይህንን ያሉት የሩሲያ የመጀመሪያ ምክትል የትምህርት ሚኒስቴር አሌክሳንደር ቡጋየቭ #ሩሲያአፍሪካ የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ እንደሆነ የሩሲያ ሚዲያ ዘግቧል። ሚኒስትሩ አክለውም ሩሲያ እና አፍሪካ የሚጋሩት የባህል፣ የሞራል እና መንፈሳዊ  እሴቶች በመኖራቸው የሩሲያ መምህራን አፍሪካ ውሰጥ ተማሪዎች ጋር ተስፋ ሰጪ የሆነ ግንኙነት አላቸው ። እያደ ያለውን የሩሲያ አፍሪካ ግንኙነት በተመለከተ ሚኒስትሩ፦ ከ50 በላይ የቋንቋ እና የሩሲያ የባህል ማእከላት በ 27 የአፍሪካ ሀገሮች መከፈታቸውን ተናግረዋል።" የእኛ የስራ ባልደረቦች በሁለተኛ ደረጃ እና በሙያ ስልጠና ጉዳይ ከሩሲያ ጋር በትብብር ለመስራት ከፍተኛ ፋላጎት አሳይተዋል። እኛም ለፍላጎታቸው መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነን።" ያሉት ሚኒስትሩ ጨምረውም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአፍሪካ ተማሪውች በሩሲያ የስነ ማስተማር ዩንቨርስቲዎች በመማር ላይ ናቸው።ሚኒስትሩ ተስፋ ሰጪ ሰለሆኑ የትብብር መስኮች ሲያብራሩ አዳዲስ የሩሲያ ትምህርት ማእከላትን አጋር በሆኑ ሀገሮች መክፈት ፤ የትምህረት ስርአቱን የሚያግዙ ፕሮፌሽናል ኮርሶችን ማዘጋጀት ላይ የሚደረግ እገዛ እና ደጋፊ የሆነ የስነ ማስተማር ድጋፍ ማድረግ የተለዩ የትብብር ምኮች ናቸው።"ትኩረት መስጠት የምፈልገው ሁሌም ቢሆን አብሮ ለመስራት እና ለማገዝ ዝግጁ መሆናችንን ነው። ለአጋሮቻችን ምስጋና አለን አብረውን ለመስራት ዝግጁ ስለሆኑ።" በማለት ምክትል ሚኒስትሩ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0