ዛሬ ላይ የሩሲያ መንግስት ከ33 የአፍሪካ ሀገራት ጋር የወታደራዊ ቴክኒካል ትብብር ስምምነት ፈርሟል የሩስያ ፕሬዝደንት አማካሪ የ #ሩሲያአፍሪካ ኮንፈረስ አዘጋጅ ኮሚቴ ፀሀፊ አንቶን ኮብያኮቭ ተናገሩ ኮብያኮቭ በኮንፈረንሱ ጎንዩሽ ላይ እንዳሉት፦◽ ሩሲያ በቅርብ ግዜ በሴኔጋል እና በታንዛንያ የንግድ ቢሮዎችን ትከፍታለች። ◽ የምእራቡ አለም የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት ዝግጁ አይደለም ይልቅ ውጥረትን ማባባስ ላይ ይሰራል።◽ሩሲያ በጋሚቢያ፣ ላይቤሪያ ፣ የኮሞሮስ ህብረት እና ቶጎ ሌሎች ሀገራት ኤምባሲዎች ለመከፈት እቅድ አላት።◽ሩሲያ ከቅኝ ግዛት ድርጊቶች እና አስተሳሰቦች ነፃ መውጣት የሚፈልጉ የአፍሪካን ሀገሮች እውቅና በመስጠት ትደግፋለች።◽ አዲስ ራሱን የቻለ የገንዘብ ስረአት ለአፍሪካ ሀገሮች በ2030 ለመፍጠር አስባለች።◽ የ #ሩሲያአፍሪካ የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ 54 ተወካዩች እና 45 ሚኒስትሮች ተሳትፈውበታል።◽ ከ1500 በላይ ሰዎች በመጀመሪያው የ #ሩሲያአፍሪካ የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ ተሳትፈዋል◽ የ #ሩሲያአፍሪካ ኮንፈረንስ በቋሚነት ሊደረግ ታስቧል።◽ ሩሲያ መጠነ ሰፊ የሆነ ግንኙነት እና ትብብር ከአፍሪካ ሀገራት ጋር እየመሰረተች ነው የፀጥታውን ዘርፍ ጨምሮ◽በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት በሩሲያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ የአፍሪካ ተማሪዎች ቁጥር አሁን ካለበት 33,000 ወደ 46,000 ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።◽ ብዙ የሁለትዮሽ ስምምነቶች በሀገራት መሀከል የሚደረጉ ስምምነቶች በ #ሩሲያአፍሪካ የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ወቅት ይፈረማሉ።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
ዛሬ ላይ የሩሲያ መንግስት ከ33 የአፍሪካ ሀገራት ጋር የወታደራዊ ቴክኒካል ትብብር ስምምነት ፈርሟል የሩስያ ፕሬዝደንት አማካሪ የ #ሩሲያአፍሪካ ኮንፈረስ አዘጋጅ ኮሚቴ ፀሀፊ አንቶን ኮብያኮቭ ተናገሩ
10:26 10.11.2024 (የተሻሻለ: 10:44 10.11.2024)
ሰብስክራይብ