የሩሲያ እና የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስለ መካከለኛው ምስራቅ እና የሰሀራ-ሳህልን የተመለከቱ ጉዳዩች ላይ መወያየታቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቀ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ እና የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስለ መካከለኛው ምስራቅ እና የሰሀራ-ሳህልን የተመለከቱ ጉዳዩች ላይ መወያየታቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቀበሩሲያው ሰርጌ ላቭሮቭ እና የአልጄሪያ አቻቸው አህመድ አታፍ መካከል የተደረገው እና የተነሱት ሀሳቦች በሚስጥር የተያዙበት ውይይት ፤ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ቀጠናዊ እና አለምአቀፋዊ  ጉዳዩች ላይ ሲሆን መካከለኛው ምስራቅን እና የሰሀራ-ሳህል አካባቢ ላይ የተለየ ትኩረት ማድረጉ ተገልጿል።  ይህ ስብሰባ ሶቺ ውስጥ እየተደረገ ያለው #ሩሲያአፍሪካ  ሚኒስትሮች አጋርነት ፎረም የጎንዮሽ ስብሰባ አንዱ ነው።"ወቅታዊ ጉዳዩች እና በሩሲያ እና በአልጄሪያ መሀከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ላይ በጥልቀት ለመስራት ተነጋግረናል። በተመሳሳይ በሀገራቱ ከፍተኛ ልኡካን መሀከል ያለው ግብብነት በተመድ የፀጥታ ምክርቤት ውስጥ ጭምር አርኪ ነው" እንደ ዘገባው ከሆነ።በአለም አቀፍ ህግ መርህ እና የተመድ ስምምነቶች መሰረት ግጭቶችን ለመፍታት በዋናነት በፖሎቲካ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ብቻ መሆን እንዳለበት በውይይቱ ወቅት ትኩረት ተሰጥቶበታል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0