🪧 በተባባሰው የሞዛምቢክ የምርጫ ውጤት ተቃውሞ ከ20 ያላነሱ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ የገዥው ፍሬሊሞ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ቻፖ፤ መስከረም 29 በተካሄደው የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 70.67% ድምጽ በማግኘት እንዳሸነፉ መገለጹን ተከትሎ፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቷል። ሆኖም፤ ሀገሪቱን ሸሽተው ወጥተዋል በሚባሉት ፕሬዝዳንታዊ እጩ ቬናንሢዮ ሞንድላኒ የሚመራው የተቃዋሚ ፓርቲ፤ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ወጤቱን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፤ ትክክለኛው የምርጫ ውጤት እስኪመለስ ድረስ ተከታታይ አድማ እና ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል። ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች መሞታቸውን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ መቁሰል ወይም መታሰራቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሪፖርት አድርገዋል። ለተቃውሞ የወጡ ሶስት ሰዎች እንደተገደሉ እና 66 ሰልፈኞች ላይ ጉዳት መድረሱን፤ የማፑቶ ማዕከላዊ ሆስፒታል ሐሙስ እለት አረጋግጧል። የፍሬሊሞ ባለስልጣናት፤ ህዝባዊ ተቃውሞው ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት እና “የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ” ነው በማለት አውግዘውታል። በብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣብያ ቀርበው ንግግር ያደረጉት የፍሬሊሞ ቃል አቀባይ አልሲንዳ ዴ አብሩ፤ የቀጠለው የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ እንዳሳሰባቸው በመግለፅ፤ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፎች አመፅ የሚያበረታቱ እና መንግሥትን የማተራመስ ዓላማ ያላቸው ናቸው ብለዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
🪧 በተባባሰው የሞዛምቢክ የምርጫ ውጤት ተቃውሞ ከ20 ያላነሱ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ
🪧 በተባባሰው የሞዛምቢክ የምርጫ ውጤት ተቃውሞ ከ20 ያላነሱ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ
Sputnik አፍሪካ
🪧 በተባባሰው የሞዛምቢክ የምርጫ ውጤት ተቃውሞ ከ20 ያላነሱ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ የገዥው ፍሬሊሞ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ቻፖ፤ መስከረም 29 በተካሄደው የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ 70.67% ድምጽ በማግኘት እንዳሸነፉ መገለጹን ተከትሎ፤... 08.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-08T19:36+0300
2024-11-08T19:36+0300
2024-11-08T20:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
🪧 በተባባሰው የሞዛምቢክ የምርጫ ውጤት ተቃውሞ ከ20 ያላነሱ ሰዎች መሞታቸው ተነገረ
19:36 08.11.2024 (የተሻሻለ: 20:04 08.11.2024)
ሰብስክራይብ