አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በብሪክስ ማዕቀፍ የሩሲያ አፍሪካ ኔትዎርክ ዩኒቨርሲቲዎችን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀረበለት

ሰብስክራይብ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በብሪክስ ማዕቀፍ የሩሲያ አፍሪካ ኔትዎርክ ዩኒቨርሲቲዎችን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀረበለት ጥሪው የቀረበው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ፤ ከሩሲያ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ቆስጠንጢኖስ ሞግሌብስኪ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ከሩሲያ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቴክኖሎጂ፣ ሕክምና፣ ጠፈር ሳይንስ፣ ፊዚክስ እንዲሁም በማዕድን እና ኢነርጂ ዘርፎች የላቀ ትብብር በሚመሰረትበት መንገድ ዙርያ ምክክር አድርጓል። የሩሲያው ሚኒስትር በዚህ ወቅት ዩኒቨርሲቲው ወደ ሙሉ ራስገዝነት የሚያደረገውን የሽግግር ሂደት እንደሚደግፉ አስታውቀዋል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የብሪክስ ዩኒቨርሲቲዎች ህብረት አባል ነው። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0