ታሊባን የትራምፕን በድጋሚ መመረጥ ተከትሎ ከአሜሪካ የሽብርተኝነት መዝገብ እንደሚነሳ ተስፋውን ገለጸ

ሰብስክራይብ
ታሊባን የትራምፕን በድጋሚ መመረጥ ተከትሎ ከአሜሪካ የሽብርተኝነት መዝገብ እንደሚነሳ ተስፋውን ገለጸበኳታር የታሊባን* የፖለቲካ ቢሮ ኃላፊ ሱሄል ሻሄን “ጦርነቱ ባበቃበት እና አዲስ ምዕራፍ ላይ ባለንበት ወቅት አባላቶቻችንን በዚህ ዝርዝር ውስጥ ማቆየቱ ምንም ፋይዳ የለውም” ሲሉ ለስፑትኒክ አርብ ዕለት ተናግረዋል። ከ2017 እስከ 2021 በነበረው የትራምፕ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን፤ አሜሪካ እና ታሊባን ጦርነታቸውን እንዳቆሙ እና የአሜሪካ ጦር በአፍጋኒስታን የነበረው ቆይታ እንዲያበቃ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ የፖለቲካ ቢሮ ኃላፊው አስታውሰዋል። በ1999 የፀደቀው የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ቁጥር 1267፤ ታሊባን ኦሳማ ቢን ላደንን አሳልፎ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ሲሆን፤ ታሊባን ጥያቄውን እስኪቀበል ድረስ ሁሉም ሀገራት ማዕቀብ እንዲጥሉ መመሪያ ሰጥቷል።*ታሊባን በሩሲያ እና በተለያዩ ሀገራት የተከለከለ አሸባሪ ቡድን ነው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0