ኢትዮጵያ ለድንበር ተሻጋሪ የመንገድ ግንባታ የሚሆን 738 ሚልየን ዶላር ብድር ለደቡብ ሱዳን ልትሰጥ እንደሆነ ተገለጸ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለድንበር ተሻጋሪ የመንገድ ግንባታ የሚሆን 738 ሚልየን ዶላር ብድር ለደቡብ ሱዳን ልትሰጥ እንደሆነ ተገለጸ ፕሮጀክቱ፤ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን ግኑኝነት እንደማያሻሽል እና የሁለቱን ሀገራት ትስስር ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል። 220 ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው የመንገድ ግንባታ ላይ፤ ኢትዮጵያውያን መሐንዲሶች እንደሚሳተፉ፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። ኢትዮጵያ፤ ለደቡብ ሱዳን ልትሰጥ ያሰበችው ብድር የአራት ዓመት እፎይታ ጊዜን ያካተተ ሲሆን፤ በአስር ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚመለስ እንደሆነ ዘገባው አክሏል። በሁለቱ የአፍሪካ ሀገራት የተደረሰው ስምምነት፤ በ2023 እንደተፈረመ ተዘግቧል። የሁለቱ ሀገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች በሰነዱ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተሳትፈዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0