የጥቅምት 27 ምሽት አበይት የዓለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የጥቅምት 27 ምሽት አበይት የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 ጥቅምት 28 ፑቲን ንግግር የሚያደርጉበት የቫልዳይ ክለብ ስብሰባ መሪ ቃል፤ "የጋራ ደህንነት እና እኩል የልማት እድሎች በ21ኛው ክፍለ ዘመን" እንደሚሆን ክሬምሊን አስታወቀ። 🟠 ጆ ባይደን እና ካማላ ሃሪስ ዴሞክራቶች በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መሸነፋቸውን እንደተቀበሉ ለመግለፅ፤ ለትራምፕ ስልክ ለመደወል በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የዋይት ሀውስ ምንጮችን ጠቅሶ የአሜሪካ ሚዲያ ዘግቧል። 🟠 የዩክሬን ጦር ኢኖርጎዳር እና ዛፖሮዢያ ኒውክሌር ሃይል ጣቢያ አቅራቢያ በሚገኘው የባህር ዳርቻ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት እንዳደረሱና ቢያንስ 5 ፍንዳታዎች መዘገባቸውን፤ ሆኖም የአየር መቃወሚያዎች ስራቸውን እየሰሩ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተናገሩ። 🟠 የእስራኤል አየር ሃይል በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻ በሚገኝ የመኖሪያ አካባቢዎች ተከታታይ ጥቃት ፈጽሟል። 🟠 በአሜሪካ ፎኒክስ ከተማ ዳርቻ በሚገኝ አየር ማረፊያ አካባቢ አነስተኛ የንግድ ጄት በመኪና ላይ ተከስክሶ፤ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0