ዶላር በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያለአግባብ በመሳሪያነት ትቅም ላይ እየዋለ በመምጣቱ፤ ትይዩ የፋይናንስ ስርዓት ያስፈልጋል ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ገለፁ

ሰብስክራይብ
ዶላር በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ያለአግባብ በመሳሪያነት ትቅም ላይ እየዋለ በመምጣቱ፤ ትይዩ የፋይናንስ ስርዓት ያስፈልጋል ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ገለፁ "አሜሪካ በአሁኑ ሰዓት ካለችበት አደገኛ አቋም አንፃር ማንም ከዶላር አምባገነናዊነት ነፃ አይደለም። የበላይነታቸውን ለረጅም ግዜ እንደሚያጡ ስለተሰማቸው፤ በጣም የተከለከሉ ስልቶችንም ጭምር በመጠቀም ለማስቀጠል ይፈልጋሉ" ሲሉ በካዛን የ #BRICS2024 የመሪዎች ጉባኤ ውጤት ዙርያ መግለጫ የሰጡት፤ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረኪን አስጠንቅቀዋል። ብሪክስ፤ እስካሁን ከወሰናቸው ወሳኝ ውሳኔዎች፤ ከባንክ ባንክ ክፍያዎችን በሀገር ውስጥ ገንዘቦች መጠቀምን ጨምሮ፤ አማራጭ የክፍያ ዘዴዎችን ለመፍጠር መስማማቱ ነው ሲሉ የሩሲያ አምባሳደር አፅንዖት ሰጥተዋል። በፈረንጆቹ 2015 የተመሰረተው አዲስ የልማት ባንክ፤ የብሪክስ መሰረት  እንደሆነ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረኪን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት፤ የ32.8 ቢልየን ዶላር የፋይናንስ አቅም ያለው አዲስ የልማት ባንክ፤ ለመሠረተ ልማት እና ለዘላቂ ልማት ፕሮጀክቶች፤ ለብሪክስ ሀገራት ብቻ ሳይሆን፤ ለሌሎች ታዳጊ ኢኮኖሚዎችም የገንዘብ ድጋፍ ያቀርባል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0