የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የመከላከያ ሚኒስትራቸው ዮአቭ ጋላንትን አነሱ

ሰብስክራይብ
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የመከላከያ ሚኒስትራቸው ዮአቭ ጋላንትን አነሱእንደ ቤንያን ኔታንያሁ ገለጻ፤ በጋዛ ጦርነት የመጀመሪያዎቹ ወራት በእርሳቸው እና በጋላንት መካከል መተማመን የነበረ እና ውጤታማ ስራ የሰሩ ቢሆንም፤ "ከቅርብ ወራት ወዲሀ መተማመኑ ተሸርሽሯል።"ከመከላከያ ሚኒስትሩ ጋር በወታደራዊ ዘመቻው አመራር ዙርያ ከፍተኛ ልዩነት መፈጠሩንና፤ ጋላንት የመንግስትን እና የካቢኔ ውሣኔዎችን የሚቃረኑ መግለጫዎችና ድርጊቶችን ማንጸባረቃቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል። ኔታንያሁ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝን የመከላከያ ሚኒስትር አድርገው መሾማቸውን አስታውቀዋል። ኔታንያሁ አክለውም፤ ከዚህ በፊት የመንግሥት ስልጣን ይዘው የማያውቁትን ጌዲዮን ሳአር ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት እንዳጩ ገልጸዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0