የአፍሪካ ወጣቶች ደማቅ የጌም ምህዳር ለኢኮኖሚ እድገት ማነቃቂያ ነው ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ " ይህ የጌም ሥነ ምህዳር ለታላቁ ራዕያችን መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ይህም ሰዎችን ወደ መስኩ ማምጣት፣ በጌሚንግ ዘርፍ ለሚሰሩ ሰዎች ኢኮኖሚን ማሳደግ እና የዘላቂነት እና የማግኘት ሃይል የሚያስገኙ መንገዶችን የሚፍጥር ነው" ሲሉ የአፍሪካ ኢ_ስፖርት ልማት ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ እና የሞቢይሌ የጌም መድረክ ተባባሪ መስራች ሳዮ ኦዎላቢ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል ።ኦዎላቢ እንዳመለከቱት፣ በአፍሪካ ያለው ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር ለአዳዲስ እና ባህላዊ ጠቀሜታ ላላቸው ይዘቶች ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩ፤ እያደገ የመጣውን የጌሚኒግ ኢንዱስትሪ የሚያንቀሳቅስ ኃይል ነው። "በእርግጠኝነት 70 በመቶ የአህጉሪቱ ህዝብ በወጣትነት አድሜ ክልል ውስጥ ይገኛል። እናም በእነዚህ የቪዲዮ ጨዋታዎች ውስጥ የተሳተፉ ማንኛውም ሰዎች ካሉ በእርግጠኝነት ወጣቶች መሆናቸውን ማወቅ ይቻላል" ብለዋል።በተጨማሪም ለአካባቢው ጠቀሜታ ያለው የጌም ይዘት እንዲፈጠር የሚያስችሉ የፋይናንስ ፕሮግራሞችን እና ፖሊሲዎችን ጨምሮ ደጋፊ ሥነ-ምህዳር ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑን አጽንዕኦት ሰጥተዋል።የኢ-ስፖርቶች ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና እየጨመረ መምጣቱ እና የኦሎምፒክ ኢ-ስፖርት ጨዋታዎች መካተታቸው፤ ለአፍሪካ ጌመሮች እና ጌም አብልጻጊዎች ዓለም አቀፍ እውቅናን እንዲያገኙ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር የጠቆሙት ባለሙያው ለዚህም አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ።"አበልጻጊ፣ አሳታሚ፣ ጌመር ወይም በሥነ-ምህዳሩ ውስጥ የሚያደርጉት ሌላ ማንኛውም ነገር ቢሆንም አፍሪካውያን እንዲያድጉ እድሎችን እና መድረኮችን እየፈለግኩ ነው። እኔ የምፈልገው ይህን ነው፤ እናም በአለም አቀፍ ደረጃ በጌም ስነ-ምህዳሩ ውስጥ ድምጽ የሚሆኑ ብዙ ሰዎች ለእኛ እንደሚናገሩ እና እንደሚረዱን ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የአፍሪካ ወጣቶች ደማቅ የጌም ምህዳር ለኢኮኖሚ እድገት ማነቃቂያ ነው ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ
የአፍሪካ ወጣቶች ደማቅ የጌም ምህዳር ለኢኮኖሚ እድገት ማነቃቂያ ነው ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
የአፍሪካ ወጣቶች ደማቅ የጌም ምህዳር ለኢኮኖሚ እድገት ማነቃቂያ ነው ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ " ይህ የጌም ሥነ ምህዳር ለታላቁ ራዕያችን መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ይህም ሰዎችን ወደ መስኩ ማምጣት፣ በጌሚንግ ዘርፍ ለሚሰሩ ሰዎች ኢኮኖሚን... 04.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-04T13:50+0300
2024-11-04T13:50+0300
2024-11-04T14:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የአፍሪካ ወጣቶች ደማቅ የጌም ምህዳር ለኢኮኖሚ እድገት ማነቃቂያ ነው ሲሉ ባለሙያው ተናገሩ
13:50 04.11.2024 (የተሻሻለ: 14:04 04.11.2024)
ሰብስክራይብ