የተቃዋሚው ፓርቲ ድል በቦትስዋና 'እዚህ እያየን ያለው ልዩ የሆነ የስልጣን ሽግግር ነው ኤክስፐርቶች

ሰብስክራይብ
የተቃዋሚው ፓርቲ ድል በቦትስዋና 'እዚህ እያየን ያለው ልዩ የሆነ የስልጣን ሽግግር ነው ኤክስፐርቶች ቦትስዋና ታሪካዊ የሆነ የፖለቲካዉን ዳራ እየቀየረ ያለ የስልጣን ሽግግር እያካሄደች ነው። ላለፈው 58 አመት ሀገሪቱን ያስተዳደረው የቦትስዋና ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በዱማ ቦኩ ለሚመራው ተቃዋሚው ጥላ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ  ፓርቲ  ስልጣኑን እያሰረከበ ነው። ጥላ ከ61 ምርጫ ጣቢያዎች 36ቱን በማሸነፍ  ለስድስት አስርት አመታት የቆየውን አመራር ለመቀየር ጫፍ ደርሷል።  "በሰላማዊ እና በግልፅ ማንም ሰው በሚያየው መልኩ ከአንድ መንግስት ወደ ሌላ መንግስት የሚደረግ የስልጣን ሽግግር ነው የሚሆነው። በተገለፀው ምክንያት እዚ እየተደረገ ያለው በጣም ወሳኝ ነው። ይህም በአፍሪካ ውስጥ ቦትስዋናን በዲሞክራሲያዊ ሀገርነት እየመራች መሆኑን ያሳያል።" ኤርነስት ሞሎ የቦትስዋና ጋርዲያን እና ሚድዊክ ሰን ጋዜጣ ምክትል ዋና ኤዲተር እንዲሁም የፓን-አፍሪካኒስት ኦላይን ጋዜጣ መስራች ለስፑትኒክ እንደተናገሩት።እንደ ሞሎ ገለፃ አዲሱ መንግስት የሀገሪቱን ሀብት በመጠቀም በዜጎች መሀከል ያለውን የሀብት ልዩነት ማጥበብ እና  ዜጎችን ማብቃት ላይ መትጋት ይኖርበታል። የጥላ እንዲያሸንፍ የረዳው የዜጎች ማህበራዊ ደህንነት በማሰጠበቅ ዝቅተኛ የደሞዝ ወለለን በአማካኝ 300 የአሜሪካን ዶላር ከፍ ለማድረግ እቅድ መያዙ ነው።   ዜጎችን በኢኮኖሚ ማብቃት የተሰኘ ፖሊሲ አለን። ይህ ፖሊሲ ዜጎችን በሙያ፣ በፋይናስ በእውቀት እና በአስፈላጊ ግብአቶችን በመጠቀም ለማብቃት ወደ ህግ መቀየር ይኖርበታል" በማለት ጨምሮ ተናግሯል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0