ብዙ ሰዎች ለሩሲያ ያዝናሉ የእኛ ጓደኛ ያልሆኑ ምእራባውያን ሀገሮች ውስጥ የሚኖሩትን ጨምሮ ሰርጌ ላቭሮቭ

ሰብስክራይብ
ብዙ ሰዎች ለሩሲያ ያዝናሉ የእኛ ጓደኛ ያልሆኑ ምእራባውያን ሀገሮች ውስጥ የሚኖሩትን ጨምሮ ሰርጌ ላቭሮቭ" የመረጥነው የማዋሃድ እና አዲስ መስመር ፈጠራ በአለም ላይ ከፍተኛ ተቀባይነትን እያስገኘልን ነው።  በሩሲያ ላይ አግባብ ያልሆኑ እርምጃዎችን በምትወስደው አሜሪካን ውስጥ ጭምር ለእኛ የሚያዝኑ ብዙ ናቸው" የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስርጌ ላቭሮቭ እንደተናገሩት።አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ሀገራት ናፖሊዮን ጦርነት እና በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ሩሲያ ላይ መዝመታቸውን ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ የናፖሊዩን እና የሂትለር ቅንጅትም ሩሲያን ማሸነፍ አለመቻሉን በማስረዳት በአሁኑ ጦርነትም ቢሆን  አዲስ  ነገረ አይፈጠርም ብለዋል።ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከየካቲት 24, 2022 ጀምሮ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን እያካሄደች ነው።  የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኦፕሬሽኑን አስመልክቶ " በኬቭ አገዛዝ ውስጥ የዘር ማጥፋት አደጋ ለአመታት የተደቀነባቸውን ሰዎች ለመጠበቅ ነው " ብለዋል።በመስከረም መጀመሪያ ፕሬዝዳንት ፑቲን የዩክሬን መንግስት ለመደራደር ፍላጎት ካለው ሩስያ እነደማትቃወም ፤ ነገርግን ድርድሮቹ በቱርኳ ኢስታንቡል  የተደረገውን ስምምነት መሰረት ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል። ጨምረውም ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ለመደራደር ወደኋላ ብላ እንደማታውቅ ነገርግን ጊዚያዊ  ፍላጎትን ለማሳካት የሚደረግ ድርድር ውስጥ ለመግባት ዝግጁ አይደለችም ብለዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0