ኒጀር እና ሮስኮስሞስ የተባለው የሩሲያ ስፔስ ድርጅት ሶስት ሪሞት ሴንሲንግ ሳተላይት እና ራዳር ለመግዛት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ሰብስክራይብ
  ኒጀር እና ሮስኮስሞስ የተባለው የሩሲያ ስፔስ ድርጅት ሶስት ሪሞት ሴንሲንግ ሳተላይት እና ራዳር ለመግዛት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ " ከሩሲያ ድርጅት የተፈራረምነው ሶስት ሳተላይቶችን በአራት አመት ውስጥ እንዲያቀርቡልን ነው" ይህንን የተናገሩት የመገናኛ፣ ፖስታ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ሚኒስትሩ ሱዲ ሞሀመድ  ናቸው ፤ በፊርማው ስነስረአት ወቅት ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ። ሚኒስትሩ ጨምረውም ይህ ሳተላይት ኒጀር ፣ ማሊን እና ቡርኩናፋሶን ለያዘዉ ለአዲሱ የሳህል ህብረት የፀጥታ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።  የሳተላይት ጥገና ባለሙያዎችን ሩሲያ እንደምታሰለጥን ተናግረዋል። ሳተላይቱ አንዴ ከተተከለ በኋላ ሀገራቱ በተናጠል የሚያስተዳድሩት ይሆናል። ባለፈው የካቲት የሩሲያ  ስፔስ ኤጀንሲ ሮስኮስሞስ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደተናገረው፦ የአፍሪካ ሀገሮች ከሩሲያ ጋር በመተባበር የራሳቸውን ስፔስ አበልፅገው ማዘመን ይችላሉ።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0