የ2024 የአሜሪካ ምርጫ ለአፍሪካ በውሰጥም ሆነ በአለምቀፍ ደረጃ የሚለውጠው ፖሊሲ አለ ብለው እንደማያስቡ የደቡብ አፍሪካው ፕሮፌሰር ተናገሩ የጆሀንስበርግ ዩንቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ፓትሪክ ቦንድ, ሲያስረዱ ፦ ካማላ ሀሪስ ሆነ ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካን ጥቅም ሊያሰጠብቅ የሚችል ይዘት የላቸውም። "የካማላ ፕሮጀክት በኦባማ ተጀምሮ በባይደን የቀጠለ ሲሆን ለአፍሪካም ሆነ ለሶስተኛ የአለም ሀገሮች የሚያበረክተው ምንም ነገር የለም" በማለት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።እንደ የአየር ንብረት ለውጥ እና አጎዋ ከቀረጥ ነፃ እድል አይነት ጠቃሚ ፕሮጀክቶች ቢኖሩም የአፍሪካን ሀገሮችን በዘላቂነት ሊለውጥ የሚችል ትርጉም ያለው ስራ አልተሰራም ይላሉ ፕሮፌሰሩ።ከተመረጡ በ2025 የሀገሪቷን የመንግሰት አወቃቀር ለመበታተን እቅድ የያዙት የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ፤ እንደ ኤለን መስክ ያሉ ባለሀብቶች የሚደገፍ የህግ ማሻሻያ ሊያደርጉ ይችላሉ ብለዋል ፕሮፌሰሩ። ካማላ፦ በበኩላቸው የአየር ንብረት ጉዳይን በማሰቀደም የሀይል ማምረትን በተለይም የርሳቸው ደጋፊ በሆኑ ግዛቶች ላይ በማመጣጠን ሊሰሩ ይችላሉ ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ፖሊሲን በተመለከተ ካማላ ከብዙዎች ጋር አብሮ መስራትን ሲያስቀጥሉ፤ ዶናልድ ትራምፕ ራስን የማግለል ፖሊሲ ሊከተሉ እንደሚችሉ እና ይህም የአሜሪካን አለም አቀፍ ተሳትፎ የሚቀንስ ይሆናል ብለው እንደሚያስቡ ፕሮፌሰር ቦንድ ተናግረዋል። የእስራኤል እና ፍልስጤምን ግጭት በተመለከተ ካማላን በሚደግፏቸው እንደ ሚችጋን ባሉ ግዛቶች ያሉ የአረብ-አሜሪካውያንን ድጋፍ ለማግኘት ተግዳሮቶች ሊገጥማቸው ይችላል ያሉት ፕሮፌሰር ጨምረውም " አረብ-አሜሪካውያን ካማላ የፍልስጤማውያን መብት መከበር ትደግፋለች የሚል እምነት የላቸውም።" ትራምፕ በበኩላቸው " ፕሬዝዳንት ኔታንያሁ የሚጠይቁትን ሁሉ የሚሰጡ ደጋፊያቸው ይሆናሉ።" በማለት ነበር የትራምፕን የእስራኤል አጋርነት የገለፁት።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የ2024 የአሜሪካ ምርጫ ለአፍሪካ በውሰጥም ሆነ በአለምቀፍ ደረጃ የሚለውጠው ፖሊሲ አለ ብለው እንደማያስቡ የደቡብ አፍሪካው ፕሮፌሰር ተናገሩ
የ2024 የአሜሪካ ምርጫ ለአፍሪካ በውሰጥም ሆነ በአለምቀፍ ደረጃ የሚለውጠው ፖሊሲ አለ ብለው እንደማያስቡ የደቡብ አፍሪካው ፕሮፌሰር ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
የ2024 የአሜሪካ ምርጫ ለአፍሪካ በውሰጥም ሆነ በአለምቀፍ ደረጃ የሚለውጠው ፖሊሲ አለ ብለው እንደማያስቡ የደቡብ አፍሪካው ፕሮፌሰር ተናገሩ የጆሀንስበርግ ዩንቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ፓትሪክ ቦንድ, ሲያስረዱ ፦ ካማላ ሀሪስ ሆነ ዶናልድ ትራምፕ... 03.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-03T13:55+0300
2024-11-03T13:55+0300
2024-11-03T14:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የ2024 የአሜሪካ ምርጫ ለአፍሪካ በውሰጥም ሆነ በአለምቀፍ ደረጃ የሚለውጠው ፖሊሲ አለ ብለው እንደማያስቡ የደቡብ አፍሪካው ፕሮፌሰር ተናገሩ
13:55 03.11.2024 (የተሻሻለ: 14:04 03.11.2024)
ሰብስክራይብ