ኢትዮጵያ ከ156 ዓመታት በፊት በዩናይትድ ኪንግድም የተወሰደ ታሪካዊ ቅርስ ማስመለሷ ተዘገበ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ከ156 ዓመታት በፊት በዩናይትድ ኪንግድም የተወሰደ ታሪካዊ ቅርስ ማስመለሷ ተዘገበ"ከ156 ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ታሪክ ቅርስ በመጨረሻም ወደ አገር ቤት ተመልሷል። በ1868  በመቅደላ ጦርነት ወቅት የተወሰደው የአጼ ቴዎድሮስ ሁለተኛ  ጋሻ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን"  የኢትዮጵያ ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ዘግቧል። የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ጋሻውን ለማስመለስ ከአንድ ዓመት በላይ ጥረት ሲያደርግ እንደነበር ተገልጿል።  ጋሻው በ2016 ዓ.ም. ለጨረታ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም በባለስልጣኑ ጥረት እና የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጅ ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ-ሥላሴ ባደረጉት ድጋፍ  ጨረታው እንዲሰረዝ ተደርጓል።ዘገባው እንዳመላከተው፤ መጭው ትውልድ ይህን የኢትዮጵያን ታሪክ ምዕራፍ እንዲማር ጋሻው አሁን በዘላቂነት ለእይታ ይቀርባል።“ጋሻው የአገሪቱን ቅርስ ወሳኝ ክፍል የሚያመላክት እና የአፄ ቴዎድሮስን አሻራ ማሳያ በመሆኑ የቅርሱ መመለስ ለኢትዮጵያ ታሪክ ዋሳኝ ክስተት መሆኑን እንደሚያመላክት” ኢቢሲ በአጽንዖት ገልጿል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0