የጥቅምት 23 ረፋድ አበይት የአለም ዜናዎች፦

ሰብስክራይብ
የጥቅምት 23 ረፋድ አበይት የአለም ዜናዎች፦🟠 የ54 አመቱ የህግ ባለሙያ ዱማ ቦኮ ስድስተኛው የቦትስዋና ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ። 🟠 በ1986 የኢትዮጵያ እና የእንግሊዝ ጦርነት ወቅት የተዘረፈው የአፄ ቴድሮስ ሁለተኛ ጋሻ ወደ ኢትዩጵያን መመለሱን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል። 🟠 የኒጀር ባለስልጣናት የፈረንሳዩ ኦራኖ ኩባንያ በሀገሪቱ ውሰጥ ያለውን የዩራኒየም ማበልፀጊያ ለማገድ መወሰኑን ተቃወሙ፤ መግለጫውን ያወጣው በሶማር ማእድን ሰፍራ የአክሲዮን ድርሻ ያለው የኒጀሩ የመንግስት ኩባንያ ሆነው ሶፖሚን ነው።🟠 የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና አዲሱ ምክትል ፕሬዝዳንት ኪቱር ኪዲኪ የታክስ ገቢን ለመጨመር እና የኢኮኖሚ ሪፎርም ለማድረግ ቃል ገቡ። 🟠 አሚሶምን የሚተካው አዲሱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱማሊያ ሰላም አስከባሪ አርብ እለት ስራ መጀመሩን የተመድ ተወካዩች ተናገሩ። 🟠 የሩስያ ጦር 24 በሩሲያ የአየር ክልል ውስጥ የገቡ የዩክሬን ድሮኖችን መጥቶ መጣሉን መከላከያ ሚኒስቴሩ አሳወቀ። 🟠 የእስራኤል የፀጥታ ቢሮ የጦሩን እቅድ እና ሌሎች የደህነንት መረጃዎችን ሲያሾልኩ ነበር ያላቸውን በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አዋለ። እንደ ህርትዝ ዘገባ አንዱ ተጠርጣሪ የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ቢሮ የስራ ባልደረባ ሳይሆን አይቀርም። 🟠 አሜሪካን ላይ እየተደረገ ባለው የፕሬዝደንት ምርጫ 70 ሚሊዩን የሚጠጉ መራጮች ድምፅ መስጠታቸውን የፋሎሪዳ ዩንቨርሲቲ ምርጫ ላብራቶሪ አሳወቀ።🟠 በጃፓን ኬይሹ፣ ሺንኮኩ እና ኪዩቶ ደሴቶች የሚኖሩ ከ190,000 በላይ ሰዎች ከባድ ዝናብን እና የሚያስከትለውን አደጋ በመፍራት እንዲወጡ መደረጉን የጃፓን የሀገር ውሰጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ አውርዱ፦ ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0