የቦትስዋና ፕሬዝዳንት በሀገሪቱ ምርጫ መሸነፋቸውን ተቀበሉ

ሰብስክራይብ
የቦትስዋና ፕሬዝዳንት በሀገሪቱ ምርጫ መሸነፋቸውን ተቀበሉይህንንም ተከትሎ የፓርቲያቸው፤ የቦትስዋና ደሞክራሲያዊ ፓርቲ፤ የ58 ዓመት የስልጣን ዘመን እንዳበቃ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የቦትስዋናው ፕሬዝዳንት ሞግዌትሲ ማሲሲ በዚህ ሳምንት በተደረገው ምርጫ እንደተሸነፉ ማመናቸውን ተከትሎ የፓርቲያቸው፤ የቦትስዋና ዲሞክራሲዊ ፓርቲ፤ የስድስት አስርት ዓመታት የስልጣን ግዜ እንዳበቃ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።ማሲሲ ባደረጉት ንግግር "ምንም እንኳን እኔ ፕሬዝዳንታችሁ ሆኜ መቆየት ብፈልግም የህዝቡን ፍላጎት አከብራለሁ። የተመረጠውንም ፕሬዝዳንት እንኳን ደስ አለህ እላለሁ። ከሰልጣኔ በመልቀቅ አዲሱን አስተዳደር አግዛለሁ" ብለዋል።🟢የቅድመ ቆጠራ ውጤቶች እንደሚያሳዩት አዲሱ ፕሬዝዳንት ለመሆን በሂደት ላይ ባሉት ዱማ ቦኩ የሚመራው ተቃዋሚው ጥላ ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ፓርቲ በሰፊ ልዩነት ምርጫውን እየመራ ነው። የቦትስዋናው መጊ የኦላይን ሚዲያ ከ61 የምርጫ ጣቢያዎች  ያገኘው የቅርብ ግዜ ውጤት እንደሚያሳየው ጥላ የተቃዋሚ ፓርቲው  30 የፓርላማ መቀመጫዎች ሲያሸንፍ ገዢው ፓርቲ አራት ብቻ አግኝቷል።▫በሀገሪቱ የተንሰራፋው የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር በተለይም በወጣቱ ዘንድ፣ የሀገሪቱ የዳይመንድ ገበያ ማሽቆልቆል፣ የኢኮኖሚው መውደቅ እና ከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር ለገዢው ፓርቲ ሽንፈት በምክንያትነት ተጠቅሰዋል። ጥላ ለዲሞክራሲ በቅስቀሳው ወቅት ዝቀተኛ የደሞዝ ደረጃ እንደሚያስተካክል እና የማህበራዊ ፈንድን ከፍ እንደሚያደርግ ለመራጮች ቃል መግባቱን ሚዲያዎች ዘግበዋል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0