የሞሪሽየስ ፖርላማ ምርጫ ከመደረጉ 10 ቀን በፊት የማህበራዊ ሚዲያ ድረገፆችን አገደች

ሰብስክራይብ
የሞሪሽየስ ፖርላማ ምርጫ ከመደረጉ 10 ቀን በፊት የማህበራዊ ሚዲያ ድረገፆችን አገደችየመረጃ፣ መገናኛ ብዙሃን እና ቴክኖሎጂ ባለስልጣን በሀገሪቱ ያሉ የኢንተርኔት አቅራቢ ድርጅቶች እሰከ ህዳር 11 የተጣለውን ገደብ እንዲያከብሩ በመግለጫው ጠይቋል። እገዳው የተላለፈዉ ህገወጥ ይዘት ያላቸው መረጃዎች በኢንተርኔት እና በሌላ መገናኛ ዘዴዎችን እንዳይተላለፉ ለመከላከል እንደሆነ መግለጫው ጠቁሟል። ቀደም ብሎ የሞሪሺየስ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት የህግ አውጭ አካላት ምርጫው በመጪው ህዳር 10 እንደሚካሄድ አስታውቋል። ብሔራዊ ጉባኤ የሀገሪቱ ፖርላማ፤ ብሔራዊ ጉባኤ፤ በርእሰ ብሔሩ ተበትኗል።የሞሪሺየስ ብሔራዊ ጉባኤ የህግ አውጭ እና ህግ ተርጓሚ ክፍል አጠቃሎ የሚይዝ በየአምስት ዓመቱ የሚመረጡ 70 አባላት ያሉት ስብስብ ነው። 62 አባላቱ በህዝብ በቀጥታ ሲመረጡ ስምንቱ መቀመጫ ደግሞ "ምርጥ ተሸናፊ" ተብለው ከፍተኛ ድምፅ ባገኙ ነገር ግን ያላሸነፉ አባላት ይያዛል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይድ ስልኮች  APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0