የቀደሞ የሩዋንዳ ዶክተር በ1994 የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ክስ በፈረንሳይ ፍርድ ቤት 27 ዓመት ተፈረደበት

ሰብስክራይብ
  የቀደሞ የሩዋንዳ ዶክተር በ1994 የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ክስ በፈረንሳይ ፍርድ ቤት 27 ዓመት ተፈረደበትዩጄይን ሩሙሲያ ፍርዱ የተፈረደበት በወቅቱ በነበረው የዘር ማጥፋት ላይ ከተሳተፉ የሩዋንዳ ባልስልጣናት ጋር በመተባበር፣ የጸረ ቱትሲ ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት እንዲሁም የጭፍጨፋዉን ማስረጃዎች መደበቅ ላይ በመሳተፍ እንደሆነ የምእራብ የዜና ማሰራጫ ዘግቧል። በእርግጠኝነት የምነግራችሁ እኔ የጥቃት ሰለባዎች እንዲገደሉ ትእዛዝ አላስተላለፍኩም ወይም ሰለባዎች እንዲገደሉ አልፈቀድኩም በማለት ዩጄይን ክሱን ፍርድ ቤት ውሰጥ ውድቅ አድርጓል። እንደ ሪፖርቶች ከሆነ የሩሙሲያ ጠበቆች ክሱን ውድቅ ያደረጉ ሲሆን አቃቤ ህግ በበኩሉ የቀድሞ ዶክተር ላደረሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የ30 ዓመት እስራት እንዲፈረድበት ጠይቀው ነበር። እንደ ዘገባው ከሆነ ጉዳዩ የሩዋንዳን የዘር ማጥፋት በተመለከተ በፈረንሳይ ሀገር የተካሄደ ስምንተኛው ችሎት ነው።በአውሮፓውያን አቆጣጠር 1994 ሁቱዎች አነስተኛ ቁጥር ባላቸው የቱትሲ ብሄር አባላት እና ግድያው ላይ አንካፈልም ባሉ ለዘብተኛ ሁቱዎች ላይ የዘር ማጥፋት ፈፅመዋል። ከሚያዝያ እሰከ ሰኔ 1994 ከ800,000 በላይ በአብዛኛው ቱትሲና ጥቂት ቱዋ እንዲሁም ሌሎች ብሄሮች ላይ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንቡብ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይድ ስልኮች APK ፋይል ሊንከስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0