የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ቃል አቀባይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የዩክሬን ቪዛ ጉዳይ በተመለከተ ያለውን መግለጫ አዘገየ የደቡብ አፍሪካ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ሊዩን ሽራይበር ባለፈው እሁድ በሰጡት መግለጫ ከዩክሬን ጋር የዲፕሎማቲክ እና አግልግሎት ፖስፖርት ያላቸው የደቡብ አፍሪካ እና ዩክሬን ዜጎች ከቪዛ ነፃ የሆነ ጉዞ መፈራረማቸውን ለሁለቱም ሀገራት ታሪካዊ ነው ብለው ነበር። ሽራይበር ጨምረው ፕሬዚዳንት ራማፎሳ ስምምነቱን በቅርብ እንደሚያጠናቅቁ ተስፋ እንደሚያደርጉ እንዲሁም ዬክሬን የተከበረች ዋጋ ያላት የደቡብ አፍሪካ አጋር እንደሆነች አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።ነገር ግን የፕሬዝዳንት ራማፎሳ ቃል አቀባይ የሆኑት ቪንሰንት ማጋዌይና በሰጡት ፈጣን ምላሽ፤ የስምምነቱን በፕሬዝዳንቱ በጭራሽ አለመፅደቅ እንዲሁም የሽራይበርን በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ የመስጠት ሀላፊነት ጥያቄ አንሰተውበታል። "ፕሬዝዳንቱ እስካሁን ሚኒስቴሩ ከዩክሬን ጋር እንዲፈራረሙ እውቅና የሚሰጠውን ቃለጉባኤ አልፈረሙም።" ማግወይና ቀጥለውም የሽራይበርን ትክክለኛ ሂደት ያልጠበቀ አለምአቀፍ ስምምነት መግለጫ ጥያቄ አንስተውበታል። ማክሰኞ እለት የአለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስቴር ሮላንድ ላሞላ እንዳብራሩት የስምምነቱ ፅሁፉ በዲፕሎማቲክ መገናኛዎች ቢፀድቅም " እስካሁን ድረስ ስምምነቱ አልተፈረመም "። የዩክሬኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪ ሳይቢሀ ያስተናገዱት ላሞላ ለስምምነቱ የሚያሰፈልጉ ቅደመ ዝግጅቶች እየተካሄዱ እንደሆነ እና መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ስምምነቱን እንደሚያጠናቅቅ አስረድተዋል። የቀስተ ደመናዋ ሀገር ከሩሲያ ጋር የቆየ ታሪካዊ ግኑኝነት ጠብቃ ብትቀጥልም ገለልተኛ አቋምን እንደመትተድግፍ እና የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እንደምትሻ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ገልጿል፡፡ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንቡብ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይ ስልኮች APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዩጵያውያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ቃል አቀባይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የዩክሬን ቪዛ ጉዳይ በተመለከተ ያለውን መግለጫ አዘገየ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ቃል አቀባይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የዩክሬን ቪዛ ጉዳይ በተመለከተ ያለውን መግለጫ አዘገየ
Sputnik አፍሪካ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ቃል አቀባይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የዩክሬን ቪዛ ጉዳይ በተመለከተ ያለውን መግለጫ አዘገየ የደቡብ አፍሪካ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ሊዩን ሽራይበር ባለፈው እሁድ በሰጡት መግለጫ ከዩክሬን ጋር የዲፕሎማቲክ እና... 01.11.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-11-01T14:49+0300
2024-11-01T14:49+0300
2024-11-01T15:24+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ራማፎሳ ቃል አቀባይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የዩክሬን ቪዛ ጉዳይ በተመለከተ ያለውን መግለጫ አዘገየ
14:49 01.11.2024 (የተሻሻለ: 15:24 01.11.2024)
ሰብስክራይብ