የጥቅምት 21 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፡-

ሰብስክራይብ
የጥቅምት 21 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፡-🟠 የደቡብ አፍሪካ መንግሥት በመጪዎቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የበጀት ጉድለት እና ዕዳ እንደሚኖር ተነበየ፡፡🟠 የቦትስዋና ፓርላማ ምርጫን ገዥው ፓርቲ በመምራት ላይ እንደሚገኝ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ።🟠 የአልማዝ ፍላጎት በመቀነሱ እና በከፍተኛ ድርቅ ምክንያት የናሚቢያ ዓመታዊ የኤኮኖሚ ዕድገት ትንበያ ዝቅ እንዳለ የሀገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡🟠 ታንዛኒያ እና ዛምቢያ ለታንዛኒያ-ዛምቢያ የባቡር መስመር ፕሮጀክት የግል ባለሀብቶችን እያፈላለጉ እንደሆነ ተገለጸ።🟠 በዛፓሮዢይ ክልል በዩክሬን ጦር ሃይሎች በተፈጸመ የሽብር ጥቃት ሶስት ሰዎች ጉዳት ደርሰባቸው።🟠 የሩሲያ አየር መከላከያ ሃይል 21 የዩክሬን ድሮኖችን እንዳወደመ የመከላከያ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።🟠 እስራኤል በምስራቃዊ ሊባኖስ ባካሄደችው የአየር ጥቃት 19 ሰዎች ተገደሉ።🟠 ሞስኮ በሊባኖስ እና እስራኤል መካከል ሰላም ለማምጣት ዝግጁ መሆኗን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦግዳኖቭ ተናገሩ።🟠 ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል አስወነጨፈች።🟠 ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ ላስወነጨፈችው ሚሳኤል ምላሽ ለመስጠት ወታደራዊ ልምምድ እንደሚያደርጉ አስታወቁ፡፡🟠 ባይደን የሪፐብሊካን ደጋፊዎችን "ቆሻሻ" ማለታቸውን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ በቆሻሻ አንሺ መኪና ውስጥ ገብተው ቅስቀሳ አካሂደዋል።🟠 ካማላ ሃሪስ መጪውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚያሸንፉ ከሆነ አሜሪካ የባራክ ኦባማ አዲስ የስልጣን ዘመን እንደሚጠብቃት የዘ ዎል ስትሪት ጆርናል ርዕስ አንቀጽ ጠቆመ።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK  ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0