የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ተሳትፎ ስኬታማ እንደነበር የጽህፈት ቤታቸው የፕሬስ ኃላፊ ገለጹበጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ የሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን፤ በሩሲያ ካዛን በተካሄደው 16ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ መሳተፉ የሚታወስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ፤ የቡድኑ አባል ከሆነች በኋላ የተሳተፈችበት የመጀመሪያው ጉባዔ እንደሆነ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በጉባዔው ላይ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን የምክክር መድረኮች ላይ ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጋቸውን አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ማግኘት እንዳለባት እና ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓቱ እንዲሻሻል፤ በጉባዔው ጥሪ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።ከጉባዔው ጎን ለጎን፤ ከብሪክስ አባል እና አባል ለመሆን ከሚፈልጉ ሀገራት መሪዎች ጋር በተደረጉ የሁለትዮሽ ውይይቶች፤ የኢትዮጵያን አቋሞች አንጸባርቀዋል ማለታቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ተሳትፎ ስኬታማ እንደነበር የጽህፈት ቤታቸው የፕሬስ ኃላፊ ገለጹ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ተሳትፎ ስኬታማ እንደነበር የጽህፈት ቤታቸው የፕሬስ ኃላፊ ገለጹ
Sputnik አፍሪካ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ተሳትፎ ስኬታማ እንደነበር የጽህፈት ቤታቸው የፕሬስ ኃላፊ ገለጹበጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራ የሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን፤ በሩሲያ ካዛን በተካሄደው 16ኛው የብሪክስ የመሪዎች... 29.10.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-10-29T11:06+0300
2024-10-29T11:06+0300
2024-10-30T14:04+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ተሳትፎ ስኬታማ እንደነበር የጽህፈት ቤታቸው የፕሬስ ኃላፊ ገለጹ
11:06 29.10.2024 (የተሻሻለ: 14:04 30.10.2024)
ሰብስክራይብ