እስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን በተቻለ ፍጥነት እንድታቆም ፈረንሳይ ጠየቀችየፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት በሊባኖስ እና በጋዛ ሰርጥ ያለውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ " ማክሮን እስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን በተቻለ ፍጥነት እንድታቆም ጠይቀዋል" ብሏል።ፈረንሳይ የሊባኖስን ህዝቦች እና የሀገሪቱን መሰረታዊ ተቋማት ለማገዝ በቅርቡ ጉባኤ እንደምታዘጋጅም መግለጫው አክሎ ገልጿል።ፓሪስ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 1701 በጥብቅ በማክበር የሊባኖስ ግዛት አንድነት እንዲከበር ትፈልጋለች ሲል መግለጫው አመልክቷል። ማክሰኞ ኢራን ወደ ደቡባዊ እና መካከለኛው እስራኤል 400 የሚጠጉ ሚሳኤሎችን መተኮሷ ተዘግቧል። የኢራን አይአርጂሲ በይፋ ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ እስራኤል በሃማስ የፖለቲካ ቢሮ ሊቀመንበር ኢስማኢል ሃኒዬህ እና በሂዝቦላህ ዋና ፀሃፊ ሀሰን ናስራላህ ላይ ለፈጸመችው ግድያ ምላሽ ነው ብሏል።ኢራን በእስራኤል ላይ የወሰደችው እርምጃ አብቅቷል፣ነገር ግን እስራኤል ግጭት ብትቀስቀስ ምላሹ የበለጠ ጠንካራ ይሆናል ሲሉ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናግረዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
እስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን በተቻለ ፍጥነት እንድታቆም ፈረንሳይ ጠየቀች
እስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን በተቻለ ፍጥነት እንድታቆም ፈረንሳይ ጠየቀች
Sputnik አፍሪካ
እስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን በተቻለ ፍጥነት እንድታቆም ፈረንሳይ ጠየቀችየፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት በሊባኖስ እና በጋዛ ሰርጥ ያለውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ " ማክሮን እስራኤል ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን በተቻለ ፍጥነት... 02.10.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-10-02T14:26+0300
2024-10-02T14:26+0300
2024-10-02T14:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий