በየመን አል ሁዳይዳህ ከእስራኤል በተሰነዘረ ጥቃት አራት ሰዎች ሲሞቱ 40 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ

ሰብስክራይብ
  በየመን አል ሁዳይዳህ ከእስራኤል በተሰነዘረ ጥቃት አራት ሰዎች ሲሞቱ 40 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ" እሁድ አል ሁዳይዳህ ላይ ጽዮናውያን ወረራዎች የፈጸሙት ጥቃት ለአራት ንፁሀን ዜጎች ሞት እና ለ40 ሰዎች መቁሰል ምክንያት ሆኗል" ሲል አልማሲራህ ብሮድካስቲንግ የሀገሪቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጠቅሶ ዘግቧል። ጥቃቱ የተካሄደው በቅርቡ ሁቲዎች በእስራኤል ላይ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ መሆኑን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል። እሁድ እለት ቀደም ብሎ የግዛቱ አስተዳደር ምንጭ ለ ስፑትኒክ እንደተናገረው የእስራኤል ተዋጊ ጄቶች በአል ሁዳይዳህ ላይ ተከታታይ ጥቃት ፈጽመዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0