ኢትዮጵያውያን በበርሊን ማራቶን አሸናፊ ሆኑ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያውያን በበርሊን ማራቶን አሸናፊ ሆኑ‍ በወንዶች የማራቶን ውድድር ሚልኬሳ ​​መንገሻ 2፡03፡17 በመግባት አንደኛ በመሆን አጠናቅቋል። የገባባት ሰዓት የግሉ ምርጥ ሰዓት ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፤ መንገሻ በመጨረሻዎቹ ኪሎ ሜትሮች ላይ የኬንያውን ሳይፕሪያን ኮቱትን አምስት ሰከንድ ብቻ ሲቀው ነው አልፎት የሄደው። "ለዚህ ውድድር በጣም ጠንካራ ልምምድ ሳደረግ ነበር። ሜዳማ ስለሆነ ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ እንደምችል ገምቼ ነበር " ማለቱን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ከዚህ ቀደም በለንደን ማራቶን ፈታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙትም ቁርጠኝነቱ በበርሊን ውጤት አስገኝቶለታል።‍ በሴቶች ፉክክር ሌላ አስደናቂ ውጤት በትግስት ከተማ ተመዝግቧል፤ ትዕግስት 2፡16፡42 በመግባት አሸናፊ ስትሆን፤  መስታወት ፍቅር እና ቦሰና ሙላቴ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን ውድድሩ በኢትዮዽያውያን አትሌቶች የበላይነት እንዲጠናቀቅ አስችለዋል። የትዕግስት ከተማ ሰዓት በውድድሩ የተመዘገበ ሶስተኛው ፈጣን ጊዜ ሆኖ ተመዝግቧል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0